ምስጢረ ስላሴ ክ. 1

 #ምስጢረ #ሥላሴ


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም።


 ክፍል 1

ከዚህ ቀደም በነበረን መርሃ-ግብር 

ምስጢረ ስላሴ ለምን ሚስጢር እንደተባለ መመልከታችን የሚታወስ ነው። ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ስላሴ ምንነትና መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ስላሴ ምን ይላል የሚሉትን እንመለከታለን።

✟...እግዚአብሔርየሁላችንንም ልቦና ያብራ!

(ማሳሰቢያፅሁፉ ረዘም ቢልም በትዕግስት እንዲያነቡት በእግዚአብሔር ስም እንለምናለን)

ሥላሴየሚለው ቃል ‹‹ ሰለሰ ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በአማርኛ ሶስትነት ማለት ነው፡፡ ሦስትነት ማለት አንዱ እግዚአብሔር በሶስት አካል ያለ አምላክ ማለት ነው። 

አካል ማለት ""እራሱን የቻለ እኔ የሚል ህላዌ ያለው፣ ራሱን #እኔ ብሎ መጥራት የሚችል በሌሎችም #አንተ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ህያው የሆነ፣ እንዲሁም ስሜት (emotion)እና እውቀት ያለው አካል ይባላል።(ኪዳነወልድ ክፍሌ መፅሀፈ ሰዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ ገፅ 218(፪፻፲፰)

በአጠቃላይየምስጢረ ሥላሴ ትምህርት የእግዚአብሔርን አንድነትና ሶስትነት የምንማርበት ትምህርት ነው፡፡

➫የእግዚአብሔር ሶስትነት፦ የእግዚአብሔር ሶስትነት በአካል፣ በግብር፣ በስም ናቸው።

የአካል ሶስትነት፦ አካል ማለት ከላይ ለመግለፅ እንተሞከረው ""እራሱን የቻለ እኔ የሚል ህላዌ ፣ ራሱን #እኔ ብሎ መጥራት የሚችል በሌሎችም #አንተ ተብሎ ሊጠራ የሚችል ህያው የሆነ፣ እንዲሁም ስሜት (emotion)እና እውቀት ያለው አካል ይባላል።አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እንደተረጎሙት

ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን አብ የራሱ የሆነ ፍፁም አካል ወልድ የራሱ የሆነ ፍፁም አካል መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ ፍፁም አካል አላቸው ብላ ታስተምራለች። እንደሚከተለው በስፋት እንመልከተው፦

✟👉አብ፦ "እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

"(የማቴዎስወንጌል 3:17፤)ከዚህ ቃል በመነሳት አካል የሚለውን እንረዳው ➫ልጄ ማለት ትርጉሙ የእኔ ልጅ እንደማለት እንደሆነ በግልፅ ይታወቃል ስለዚህ በተዛዋሪ እግዚአብሔር አብ #እኔ ብሎ እራሱን ጠርቷል፤ ስለዚህም ➫እራሱን እኔ ብሎ መጥራት የሚችል የሚለው ትርጉም በዚህ እንረዳለን ማለት ነው። በማስከተልም የራሱ የሆነ ስሜት ያለው የሚለው ትርጉም ላይ እግዚአብሔር አብ ወልድን #የምወደው እያለ ስሜቱን ሲናገር እንመለከታለን ስለዚህ አብ የራሱ የሆነ ስሜትም አለው ማለት ነው። ስለዚህ አብ የስላሴ አንድ አካል።

✟👉ወልድ፦ 

"58፤ ኢየሱስም። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።"

(የዮሐንስወንጌል 8:58፤)ይህ ቃል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድመ አለም ለመኖር አንዱ ማስረጃ ሲሆን ቅድመ አለም ለመኖሩም ከተናገረ ቡሃላ #እራሱን_እኔ ብሎ የመጥራቱ ነገር አካል ማለት ""እኔ ብሎ መጥራት የሚችል"" ለሚለው ትርጓሜ ሲያስኬድ ቅድመ አለም በአካልነት ለመኖሩም ትልቅ ማስረጃ ነው።

✟👉 መንፈስ ቅዱስ፦ "22፤ መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።" (የሉቃስወንጌል 3:22፤)

ማጠቃለያ፦ ከእነዚህ እንደምንረዳው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የራሳቸው ፍፁም አካል እንዳላቸው ነው ስለዚህ በአካል ሶስት ናቸው ነው እንላለን!

የስምሶስትነት፦  የስም ሶስትነት ማለት የየራሳቸው መታወቂያ ስም ያላቸው ማለት ነው። ለዚህም በወንጌል

"19-20፤ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥

"(የማቴዎስወንጌል 28:19-20፤)ከዚህ ቃል የምንረዳው አብ የራሱ የሆነ የተለየ ስም ወልድ የራሱ የሆነ የተለየ ስም መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ የተለየ ስም እንደሆነ ነው። ይህም የስም ሶስትነት ይባላል።

✟➫የእግዚአብሔር አንድነት

አንድነት ማለት በሶስት አካል የተገለፀው አምላክ አንድ የሚሆንበት ማለት ነው።

➫የእግዚአብሄር አንድነት በባሕርይ ፣በመፍጠር ፣በስልጣን ፣በአገዛዝ ፣በመለኮት ፣በፈቃድ ፣በህልውና (በአኗኗር)እና የመሳሰሉት ናቸው።

✟➫ባህሪ፦ ባህሪ ማለት የእግዚአብሄር መገለጫው ማለት ነው። በስላሴነት የሚኖረው እግዚአብሄር ሶስቱ አካል የባሕርይ አንድነቱም፦ ቅድስና፣ ሁሉን አዋቂነት፣ ፅድቅ፣ ፍቅር፣ ሁሉን ቻይነት፣ ምሉዕነት፣ ዘለአለማዊነት ናቸው። ከዚህ በላይ የተመለከትንው በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን የእግዚአብሔር ባህሪያት ብላ ትምህርተ ሃይማኖት በተሰኘው የትምህርት ክፍል ውስጥ በህልወተ እግዚአብሄር ስር የሚሰጥ ሰፊ ትምህርት ነው እያንዳንዱንም እንደሚከተለው እንመለከታለን

1✟👉ቅድስና:-

➫አብ:-"...ቅዱስ አባት ሆይ..."

(የዮሐንስወንጌል 17:11፤)

ዩሀንስወንጌል 17:11

➫ወልድ:-

"...ቅዱስናያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት..."

(ወደዕብራውያን 7:26፤)

➫መንፈስቅዱስ፦ "ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን #ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።"

(ወደኤፌሶን ሰዎች 4:30፤)

2✟👉ሁሉንአዋቂነት፦

➫አብ፦ "...የሰውንልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው። "

(መጽሐፈነገሥት ቀዳማዊ 8:39፤40፤)

➫ወልድ፦ከባህር ውስጥ ከአሳ ልብ ውስጥ ያለውን በሩቅ ማወቁ የማቴዎስ ወንጌል 17:27

➫መንፈስቅዱስ፦"26፤ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን #ሁሉ ያሳስባችኋል።"

(የዮሐንስወንጌል 14:26፤)

3✟👉ፅድቅ፦ፅድቅ ማለት እውነተት ማለት ነው እግዚአብሔር ፃድቅ ነው።

➫አብ፦ 

"25፤ ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤"

(የዮሐንስወንጌል 17:25፤)

➫ወልድ፦

"እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ።"

(የዮሐንስወንጌል 14:6፤)

➫መንፈስቅዱስ፦ 

"መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።"

(1ኛየዮሐንስ መልእክት 5:7፤)

4✟👉ሁሉንቻይነት፦ 

➫አብ፦ ዘፍጥረት 35:11

➫ወልድ፦ትንቢተ ኢሳ 9:6፣ወደ ፊልጵስዮስ 3:21፣ራዕይ 1:8

➫መንፈስቅዱስ፦ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ 

ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ። 

መጽሐፈ ኢዮብ ምዕ.33

5✟👉ምሉዕነት፦ ምሉዕ ማለት በሁሉ ቦታ መገኘት ማለት ነው።

➫አብ፦ የማቴዎስ ወንጌል 11:25ላይ የሰማይና የምድር ጌታ እንደሆነ አብን ይናገራል ይህ የሚያመለክተው አብ በሰማይና በምድር እንደሚገኝና ምሉዕ እንደሆነ ነው።

➫ወልድ፦"ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።"

(የማቴዎስወንጌል 18:20)በአለም ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚሰበሰቡት ብዙ ናቸው በዚህ አለም የተበተኑ በስሙ ያመኑ ሁሉ ናቸውና። በእነዛም በመካከላቸው እሆናለሁ ብሎ በሁሉም ቦታ ምሉዕ እንደሆነ ወልድ ተናገረ ማለት ነው።

➫መንፈስ ቅዱስ፦ (መዝሙረዳዊት ምዕ.139:7-8

ከመንፈስህወዴት እሄዳለሁ?ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።

6✟👉ዘለአለማዊ፦

➫አብ፦ "እግዚአብሔርም ሙሴን። <<ያለና የሚኖር>>እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። <<ያለና የሚኖር>>ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው።"

(ኦሪትዘጸአት 3:14፤)

➫ወልድ፦

"...ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ...."

(የዮሐንስራእይ 1:18፤)

➫መንፈስቅዱስ፦


ዕብራውያን 9:14

7✟👉ፈጣሪነት፦

➫አብ፦ ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ። ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?"

(ትንቢተኢሳይያስ 44:24፤)

➫ወልድ፦"3፤ ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።"

(የዮሐንስወንጌል 1:3፤)

➫መንፈስቅዱስ፦ "የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ "

(መጽሐፈኢዮብ 33:4፤)

ማጠቃለያ፦ከዚህ በላይ ያሉትን እንዲህ መመልከት ያስፈለገው ሶስቱ የስላሴ አካል በባህሪ የተካከሉ መሆናቸውን ለማሳየት ነው ይህም አንድነታቸውን በግልፅ ያስረዳናል።

✟➫በመፍጠር፦  ከላይ እንደተነጋገርንው ሶስቱም የስላሴ አካል መፍጠር ገንዘቡ እንደሆነ ተመልክተናል በእዛም የተካከሉ እንደሆኑም ጭምር ስለዚህም በዘፍጥረት 1:1ላይ "1፤ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን #ፈጠረ።" በዚህ ቃል እንደምንረዳው  ሶስቱ የስላሴ አካላት የመፍጠር ability እያላቸው ነገር ግን የተካከሉ እኩል ስለሆኑ #ፈጠረ የሚለውን የነጠላነት የግብር ቃል ተናግሯል ማለት ነው። ስለዚህም የመፍጠር አንድነታቸውንም በፈቃድ አንድ መሆናቸውን ያመለክተናል ማለት ነው።

በቀጣይ ክፍል 2

የስላሴ አስተምህሮን የሚደግፉ ተጨማሪ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎችና ማብራሪያቸውን ይዘን እንመጣለን!


         #ወስብሐት ለእግዚአብሔር

            #ወለወላዲቱ ድንግል

             #ወለመስቀሉ ክቡር

                   #ይቆየን

Comments

Popular posts from this blog

ዕቅበተ እምነት

ወላዲተ አምላክ

መልስ ለወሒድ ዑመር