ዕቅበተ እምነት ዕቅበተ ማለት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን መጠበቅ፣ ጥበቃ የሚል የአማርኛ ትርጉም አለው።(ኪዳነወልድ ክፍሌ መፅሀፈ ሰዋሰው ወግስ መዝገበ ቃላት ሐዲስ ገፅ.705)እምነት የሚለውም ሃይማኖትን እምነትን ማለት ነው። ዕቅበተ እምነት ማለት የእምነት ጥበቃ ማለት ነው። ዕቅበተ እምነትን የሚተገብረው ሰውም ዐቃቤ እምነት ይሰኛል። ዐቅበተ እምነትን በህብረት የሚሰሩ ከሆኑም ዐቃቢያነ እምነት ይሰኛሉ። . እምነትየሚጠበቀውም ከሃሳውያን መምህራን ከሃሳውያን የፍልስፍና አራማጆች ወደ ቤተ ክርስቲያን የሀሰት ትምህርትን ሲያስገቡ መካለከልና ለእነሱም መልስን መስጠት ነው። በመፅሀፍ ቅዱሳችን አንድ ታሪክ አለ እርሱም በሐውርያት ስራ ምዕራፍ 17 ላይ የሚገኝ ነው። ብርሃነ አለም ቅዱስ ጳውሎስ ከአይሁድ ጋር ወይይቶችን ያደርግ ነበረ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስም መሲህነት ስለ ሀጢያታችን በቀራኒዮ መሰቀል ሞቶም ስለመነሳቱ ህያው አምላክ ለመሆኑም ይመስክር ነበረ። ምክንያቱም በዚያ ዘመን አይሁዶች ብዙ ክርስትናን ለማፈራረስ ይጥሩ ስለነበረ ነው፤ እርሱ ግን ብሉያትን እያጣቀሰ ይመልስላቸው ነበረ። ፧ የዐቅበተ እምነት ታሪኮች በታላላቅ ጉባኤያት ➫የኒቅያ ጉባኤ፦ ይህ ጉባኤ የተካሄደው በ318 ዓመተ ምህረት ወልድን ፍጡር ነው ብሎ የስህተት ትምህርት ያሰራጨውን አርዮስን በመፅሀፍ ቅዱስ መሰረት መልስ የተሰጠበትና፤ ከጉባኤያትም ሁሉ የላቀ ነው በጉባኤውም 318 የበቁ የነቁ የሃዋርያትን ፈለግ በተከተሉ ቅዱሳን አባቶች የእምነት ጠበቆች የተገኙበት ነው። ከእነሱም ልቆ የነበረው ዐቃቤ እምነትም በእለቱ ሊቀ ዲያቆን የነበረው ቅዱስ አትናቴዎስ ነበር። ➫የቁስጥንጥንያ ጉባኤ፦ ይህ ጉባኤ የተካሄደው በ381 ዓም በ150 ኤጲስቆጶሳት የተካሄደ ሲሆን ለዚህ ጉባኤ መካሄድ...
Comments
Post a Comment