ስቅለት በብሉይ ኪዳን!
ስለ ስቅለት በብሉይ ኪዳን
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!
ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደምድር ሲመጣ እንደ ደራሽ ውሃ በድንገት የተገለጠ አይደለም። ስለ ውልደቱ ፡ ስለ ጥምቀቱ ሆነ በምድር ላይ ስለ ሰራቸው ተአምራት በነብያት ምሳሌን እየገለጠ ፡ ትንቢት እያስነገረ የመጣ ነው። ልክ እንደዚሁ ኢየሱስ ስለ ስቅለቱም በነብያት ትንቢትን አስነግሯል ፡ ምሳሌንም ገልጧል። ምሳሌዎቹን በቅድሚያ እንመልከት እስኪ፦
➊ ዘጸአት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ እንዲህም ሆነ፤👉 #ሙሴ #እጁን #ባነሣ #ጊዜ #እስራኤል #ድል #ያደርግ #ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር።¹² የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤👉#ድንጋይም #ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ #አሮንና #ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ።
ይህ የስቅለት ምሳሌ ሲሆን ምሳሌውም፦ ሙሴ የክርስቶስ ፤ ድንጋዩም የመስቀል ፤ አሮንና ሖር የፈያታዊ ዘየማንና የፈያታዊ ዘጸጋም ፤ እስራኤል የነፍሳት ፤ አማሌቅ የአጋንንት ምሳሌ ናቸው። ይኸውም ሙሴ እጁን ባጠፈ ጊዜ እስራኤል ድል እንደመነሳታቸው ሁሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ እጁን ዘርግቶ በመልዕልተ መስቀል እስከሚሰቀል ድረስ ነፍሳት በመንጸፈ ደይን ወድቀው በእግረ አጋንንት ተጠቅጥቀው የመኖራቸው ምሳሌ ሲኾን ፤ ሙሴ እጆቹን በዘረጋ ጊዜ ግን አማሌቃውያን ድል መነሳታቸው ጌታ በዕለተ አርብ እጁን ዘርግቶ በመልዐልተ መስቀል በተሰቀለ ጊዜ አጋንንት ድል የመነሳታቸው ምሳሌ ነበር። ዳግመኛም ሙሴ እጆቹን ፀሓይ እስኪገባ ድረስ ተዘርግቶ እንደዋለ ኹሉ መድኃኒታችን ክርስቶስም እጆቹን ዘርግቶ በዕለተ ዓርብ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት በተሰቀለ ጊዜ ዓለም ኹሉ ጨለማ ኾኖ ስለመዋሉ ነው።
➋ “ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።” — ዘኍልቁ 21፥9
እስራኤላውያን እግዚአብሔርን በምድረበዳ ምግብ ማዘጋጀት ይችላልን? ሰውነታችን ይህን ጥቅም የሌለውን ምግብ ሰልችታለች በማለት እግዚአብሔርንም ሙሴንም አሙ እግዚአብሔርም ይቀጣቸው ዘንድ እየነደፈ የሚገድል እባብን ላከባቸው። እባቡም እየነደፈ ሰዎቹን በጨረሳቸው ጊዜ እስራኤላውያን ተመልሰው ወደ ሙሴ ጮኹ ሙሴም ጩኸቻቸውን ወደ እግዚአብሔር አደረሰ። እግዚአብሔርም የናስ እባብ ሰርተህ በአላማ ላይ ስቀል አለው። ይህን ጥቅስ ለስቅለት ምሳሌ መሆኑን ኢየሱስ በራሱ አንደበት ጠቅሶታል፦
“ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።”— ዮሐንስ 3፥14-15
ይህም ምሳሌው ተናዳፊው እባብ የዲያቢሎስ ፡ የናሱ እባብ ደግሞ የኢየሱስ ምሳሌ ነው። ተናዳፊው እባብ መርዝ እንዳለው ሁሉ ዲያቢሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት። የናሱ እባብ መርዝ እንደሌለበት ሁሉ ጌታ ኢየሱስም ከኃጢአት የነፃ ጽሩየ ባህሪይ ነው። የናሱ እባብ በምድራዊው(በተናዳፊው) እባብ አምሳል እንደተሰቀለ ሁሉ ኢየሱስም እንደበደለኛ ተቆጥሮ በመስቀል ተሰቅሏል። መልኩን አይተው የዳኑ በጌታ ስብከት አምነው የዳኑ ምሳሌ ሲሆኑ ፡ ድምፁን ሰምተው የዳኑ ደግሞ ከጌታ በኋላ በተነሱ መምህራን ስብከት አምነው የዳኑት የክርስቲያኖች ምሳሌ ነው።
✟ ስለ ኢየሱስ ስቅለት የተነገሩ ትንቢቶች፦
የመፅሐፍ ቅዱስን መለኮታዊነት ከምንረዳባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ከብዙ ዘመናት በፊት የተፃፉ ትንቢቶች ተፈፃሚነታቸውን ሲያገኙ በማየታችን ነው። ፍፃሜያቸውን ካገኙ ትንቢቶች መካከል ደግሞ አንዱ የኢየሱስን ስቅለት በተመለከተ የተተነበዩት ናቸው።
✟ መዝሙር 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹👉 አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህ። … ¹² ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤
¹³👉 እንደ ነጣቂና እንደሚጮኽ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ። … ¹⁶👉 ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።¹⁷👉 አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።¹⁸👉 ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።
እኒህ ሁሉ ትንቢቶች በኢየሱስ ስቅለት ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል፦
✞ አምላኬ ፡ አምላኬ ማለቱ፦ “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፦ አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።”— ማቴዎስ 27፥46
✞ ልብሶቹን ስለመከፋፈላቸው፦ “ስለዚህ እርስ በርሳቸው፦ ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም፦ ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።”— ዮሐንስ 19፥24
✟ “👉 #ጀርባዬን #ለገራፊዎች ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፥👉 #ፊቴንም #ከውርደትና #ከትፋት #አልመለስሁም።”— ኢሳይያስ 50፥6
👆 በዚህ ትንቢት ሶስት ኩነቶች በኢየሱስ ስቅለት ተፈፅመዋል ፦
➊ ጀርባዩን ስለመገረፉ በአድስ ኪዳን
“በዚያን ጊዜ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠ።”— ማቴዎስ 27፥26
“በዚያን ጊዜም ጲላጦስ ኢየሱስን ይዞ ገረፈው።”— ዮሐንስ 19፥1
➋ ፊቱን ከውርደት ስላለመለሱ በሊቀ ካህኑ ጠባቂ በጥፊ ተመታ፦
“ይህንም ሲል በዚያ ቆሞ የነበረው ከሎሌዎች አንዱ፦ ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን? ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።”— ዮሐንስ 18፥22
➌ ምራቅ ፊቱ ላይ ስለመተፋቱ፦
“በዚያን ጊዜ በፊቱ ተፉበት፤ ጐሰሙትም፥ ሌሎችም በጥፊ መትተው፦ ክርስቶስ ሆይ፥ በጥፊ የመታህ ማን ነው?”— ማቴዎስ 26፥67
" የተባለው ይፈፀም ዘንድ" እየተባሉ የተጠቀሱ ብዙ ስላሉ እነርሱን መግለፅ ፅሁፍ ማስረዘም ነው። እኒህን የሚያክሉ ጥቅሶች ባሉበት ኢየሱስ አልተሰቀለም ማለት እንዴት ይቻለናል? መልስ ለሕሊና
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
______________✝
ለማንኛውም አስተያየት፦
[ ዐቃቢያነ እምነት ዘኦርቶዶክስ ]
ለቴሌግራም ቻናላችን፦
[ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ]
Comments
Post a Comment