ስቅለት በክርስቶስ ኢየሱስ አንደበት!
ስለ ስቅለት በኢየሱስ ክርስቶስ አንደበት
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!
ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሌላው ምስክር የሚሆነን እርሱ በምድር ላይ ሳለ ወደ ፊት ስለሚፈፀምበት ነገር ያስተማረውን ቃል በማጤን ነው። ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣበት አላማ በወንጌል ላይ ግልፅ በሆነ መልኩ ተቀምጧል። እርሱም ስለ ሰዎች ልጆች ሁሉ ቤዛ ሆነ በመስቀል ላይ እንደሚሞት ነበረ። ለዚህም ጌታችን እንዲህ አለ፦ "45፤ እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና #ነፍሱን_ለብዙዎች_ቤዛ_ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።" (የማርቆስወንጌል 10:45)ኢየሱስ ክርስቶስ በእራሱ አንደበት ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ እንደሚሰጥ እየተናገረ አይ ኢየሱስ ክርስቶስ አልተሰቀለም ምስክሩ የያዛችሁት መፅሀፍ ቅዱስ ነው"" ማለት ትልቅ ቅዠት ነው።
እስኪ እራሱ ባለቤቱ ስለ ስቅለቱ ከተናገራቸው ውስጥ #የተወሰኑትን ብቻ እንመልከት፦
1-ኢየሩሳሌም ላይ ሄዶ በካህናትና በሽማግሌዎች ሞቶ በሶስተኛው ቀን እንደሚነሳ፦
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያቱ ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ ጋር የተካከለ የባህሪ ልጁ መሆኑን ከገለጠላቸው ቡሃላ ዋናውን የመጣበትን አላማ ከዚያ ቀን ጀምሮ ይነግራቸው ጀመረ ለዚህም ጌታችን ከዚህ በታች ያለውን ተናገረ
"21፤ ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።"
(የማቴዎስወንጌል 16:21)
ይህቃል የሚናገራቸው አንኳር ነገሮች ለያይተን እንመልከት፦
✟➞ወደ ኢየሩሳሌም መሔድ፦ ጌታችን የመጣበትን አላማ የሚፈፅመው በኢየሩሳሌም ከተማ ነውና ወደዚያ መሔድ ያስፈልገው ነበረ እርሱም አስቀድሞ እንደተናገረ የተናገረው ነገርም ለመፈፀሙ በማቴዎስ ወንጌል ምዕ 21 ላይ ተቀምጧል።
(የማቴዎስወንጌል ምዕ 21)
4-5፤ለጽዮን ልጅ። እነሆ፥ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።...
10#ወደ_ኢየሩሳሌምም_በገባ_ጊዜ መላው ከተማ። ይህ ማን ነው?ብሎ ተናወጠ።
ስለዚህ ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባቱ በነቢያትም የተተነበየ ሆኖ እራሱም የፈፀመው ነው።
✟➞ብዙ መከራን ተቀብሎ መሞት፦ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል እንደሚገባው አስቀድሞ ተናግሯል ይህም ስለመፈፀሙ በሊቀ ካህናቱ ግቢ ያንገላቱትና መከራን ያበረቱበት እንደነበረ በማርቆስ ወንጌል 14:65ላይ ተቀምጧል።"65፤ አንዳንዶችም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ይጐስሙትና። ትንቢት ተናገር ይሉት ጀመር፤ ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።" እንዲሁም በማርቆስ ወንጌል 15:15ላይ ዳግም በጲላጦስ ሎሌዎች መገረፉ ተገልጿል።"ጲላጦስም የሕዝቡን ፈቃድ ሊያደርግ ወዶ በርባንን ፈታላቸው፥ ኢየሱስንም ገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠ።" ከዚህም ቡሃላ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመገደሉ እንዲህ አለ፦"ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ #ነፍሱን_አሳልፎ ሰጠ።"(የዮሐንስወንጌል 19:30)
✟➞በሦስተኛውም ቀን ስለመነሳቱ፦ ጌታችን ለሃዋርያት አስቀድሞ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚሞት ከተናገረ ቡሃላ ሞትን ድል አድርጎ በሶስተኛው ቀን እንደሚነሳም ተናግሯል።
እንዲሁም እርሱ ከሞተ ቡሃላ በሶስተኛው ቀን ተነስቷል።
👉"6፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።"(የማቴዎስወንጌል 28:6፤)ያ የተናገረው ነገር ምንድነው ብንል መከራን ተቀብሎ በመስቀል ላይ ሞቶ በሶስተኛው ቀን እነሳለሁ ብሎ የተናገረው ነው።
በተጨማሪም ጌታችን በመስቀል እንደሚሞት እንደሚነሳ ስለመናገሩ
(የሉቃስወንጌል ምዕ 18)
31፤አሥራ ሁለቱንም ወደ እርሱ አቅርቦ እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ ስለ ሰው ልጅም በነቢያት የተጻፈው ሁሉ ይፈጸማል።32፤ ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታልና፥ ይዘብቱበትማል ያንገላቱትማል ይተፉበትማል፤
33፤ #ከገረፉትም_በኋላ_ይገድሉታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።
(የዮሐንስወንጌል ምዕ.12)
30፤ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። ይህ ድምፅ ስለ እናንተ መጥቶአል እጂ ስለ እኔ አይደለም።31፤ አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል፤32፤ኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ።
33፤ በምን ዓይነትም ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክታቸው ይህን ተናገረ።
እንግዲህ ከላይ እንደተመለከትንው ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እንደሚሞት ከተናገረ ከእርሱ ምስክርነት የማንም አይበልጥምና ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል አልሞተም ማለት በእውነት አይንን በጨው አጥቦ እርጥቡን ደረቅ ነው እንደማለት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
______________✝
ለማንኛውም አስተያየት፦
[ ዐቃቢያነ እምነት ዘኦርቶዶክስ ]
ለቴሌግራም ቻናላችን፦
[ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ]
Comments
Post a Comment