ኢሳይያስ 48:16

 በ 1 ድንጋይ ሶስት ወፍ= 1 ጥቅስ ለሶስት የሃይማኖት ተቋማት

      አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም

      በዚህ ጽሁፍ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በአንድት የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ሶስት የተለያዩ የሃይማኖት  ተቋማት በኢየሱስ ላይ ያላቸውን አመለካከት ኢትዮጵያ ግብፅን ዶጋሊ ላይ በደቂቃዎች የዶግ አመድ እንዳደረገቻት እኛም በደቂቃዎች የእነርሱን እምነት የዶግ አመድ እናደርገዋለን💪 😁

      መልስ የምንሰጥባቸው ሶስቱ የሃይማኖት ተቋማት፦

 1፡ እስልምና 2፡ only Jesus እና 3፡ የይሖዋ ምስክሮች ይሆናሉ ። (ጽሁፉ ሊረዝም ስለሚችል በሰከነ መንፈስ እንዲታነቡት እጠይቃለሁ )

   እኒህ ሶስቱ የእምነት ድርጂቶች እንደሚታወቀው  እርስ በእርስ የተለያዩ ሲሆኑ

 እስልምና፦ ኢየሱስ መለኮታዊ ክብር የለውም የሚሉ ሲሆን

 የይሖዋ ምስክሮች ደግሞ ፦ኢየሱስ መለኮታዊ ክብር ያለው ቢሆንም ከእግዚአብሔር አብ ጋር ግን የተስተካከለ (እኩልክብር ያለው) አይደለም ብለው የሚያምኑ ናቸው።

   Only Jesus ቤተ እምነት ደግሞ ፦ኢየሱስ እና እግዚአብሔር ወልድ የተለያዩ አካላት ሳይሆኑ አንድ አካል ናቸው። ኢየሱስ እግዚአብሔር አብ የተገለጠበት ስጋ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው።

     ሶስቱንም የሚያመሳስላቸው ነገር ደግሞ ሶስቱም ቤተ እምነቶች Unitarian መሆናቸው ነው። እንደ እነርሱ እምነት የምስጢረ ሥላሴ አስተምህሮአችን ስህተት ነው ባይ ናቸው። ከዚህ በመነሳት መልስ የምንሰጥባቸው ነገሮች 4 ናቸው ማለት ነው።  መልካም ወደ መልሱ እንሂድ፦

      መልስ ለመስጠት የምንጠቀምባት አንዲት ጥቅስ በነብዬ እግዚአብሔር ኢሳይያስ መፅሀፍ ላይ የተቀመጠችው ትሆናለች፦

      “ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።”  — ኢሳይያስ 48፥16

    በመጀመሪያ በሥላሴ ላይ ያላቸውን ምልከታ እናፍርስ፦

      ይህን የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 48ን ከመጀመሪያው ጀምረን ስናነበው እግዚአብሔር ህዝቡን ከባቢሎን በማውጣት ያደረገውን ምህረት እንመለከታለን ከቁ1 ጀምረን እያነበብን ስንወርድ በዚህ ምዕራፍ የሚናገረው አካል መለኮታዊ ባህሪያት ተጠቅሰው እናገኛቸዋለን ። ለምሳሌ ፦ ዘላለማዊት (ቁ12)፤ ምድርን መመስረቱ (ቁ13)ይነኙበታል። እኒህን ከያዝን በኋላ ከላይ ወደጠቀስነው ጥቅስ እንመለስ።  ቁ16ን ስንመለከት ያ መለኮታዊ ባህሪይ ያለው አካል እራሱን በማግለግ ሌላ መለኮታዊ ማንነት ያላቸውን ሁለት አካላት ሲጠቅስ እናያለን። በዚህ በቁ16 ላይ ሶስት የተለያዩ አካላትን እናገኛለን ማለት ነው፦ የመጀመሪያው ከቁጥር 1 ጀምሮ እየተናገረ የመጣው ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ "እግዚአብሔር " ተብሎ የተጠቀሰው አካል ነው  ፤ በሶስተኛነት ደግሞ " መንፈሱ" ተብሎ የተጠቀሰው የእግዚአብሔር መንፈስ። የእግዚአብሔር መንፈስ የተባለው ከእግዚአብሔር ጋር በአካል የተለየ ስለመሆኑ " እና" በሚል አያያዥ ቃል ከእግዚአብሔር ጋር የተለያየ ሲሆን  ከዛም በተጨማሪ ላኪ መሆኑ የራሱ የሆነ አካል ያለው እንደሆነ ያመለክተናል። 

      ከዚህ በመነሳት ሶስቱም ቤተ እምነቶች በሥላሴ አስተምህሮ ላይ ያላቸው ተቃውሞ ይፈርሳል ማለት ነው። ምክንያቱም ከዚች ጥቅስ ሶስት መለኮታዊ ማንነት ያላቸውን አካላት እናገኛለን። ይሄ ደግሞ አንድ አምላክ አንድ አካል የሚለው ይፈርሳል ማለት ነው።


    በሁለተኛነት የእስልምናን ምልከታ እናፈርሳለን፦

    በዚህ በምዕራፍ 48 ላይ ተናጋሪው አካል ከእግዚአብሔር እና ከእግዚአብሔር መንፈስ የተለየ ስለመሆኑ በግልፅ የተቀመጠ ነገር ነው። እና ይሄ አካል ማን ነው?የሚለውን ስንመለከት ኢየሱስ ሆኖ እናገኘዋለን። ለዚህ ማስረጃ የሚሆነኝን ሶስት ማሳያ ላቅርብ፦

#1ኛ፦  የመጀመሪያ ማሳያ የሚሆነኝ በምዕራፉ ውስጥ የተጠቀሱትን የአምላክ ብቻ የሆኑትን ባህሪያት ከእግዚአብሔር አብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ውጭ የሆነ ሊያሟላቸው የሚችል አካል አንድ እና አንድ እግዚአብሔር ወልድ መሆኑ ነው።

     በምዕራፉ ውስጥ የአምላክ ባህሪያት ብለን ከላይ የጠቀስናቸው ሁለት ባህሪያቶች አሉ፦

   አንደኛው "ፊተኛና ኋለኛው" (የመጀመሪያውእና የመጨረሻው/ አልፋና ኦሜጋ)ሲሆን ይህ ባህሪይ  የአንዱና የእውነተኛው አምላክ ባህሪይ ሲሆን ኢየሱስ ደግሞ ይሄንን ያሟላል። ማስረጃ፦

   “ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥”— ራእይ 1፥17

   “አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።”— ራእይ 22፥13

      ሁለተኛው በምዕራፉ የተጠቀሰው የአምላክ ባህሪይ  ደግሞ "ምድርን መመስረት እና ሰማያትን መዘርጋት" ነው። ይህም ልክ እንደላይኛው የአምላክ ስልጣን ብቻ ሲሆን ይሄንንም ኢየሱስ ሲያሟላው እናያለን። ለዚህ ማሳያ ሁለት ማስረጃዎችን ብቻ ልጥቀስ፦

      “የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥”— መዝሙር 8፥3

    “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”— ዮሐንስ 1፥3

   #2ኛ፦ ሁለተኛው ማሳያ ደግሞ በዛው ጥቅስ በቁጥር 16 ውስጥ እንዲህ የሚል ንግግር አለ ፦“ #እኔ #ከጥንት #ጀምሬ #በስውር #አልተናገርሁም፤ "  ይችን ነብዩ ያሰፈራትን ንግግር እንዳለች ኢየሱስ ሲናገራት በወንጌል ተፅፎ እናገኛለን፦ 

     “ኢየስስም መልሶ፦ #እኔ #በግልጥ #ለዓለም #ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ እኔ ሁልጊዜ አስተማርሁ፥ #በስውርም #ምንም #አልተናገርሁም።” ዮሐንስ 18፥20

     በደንብ ካነፃፀርነው የኢየሱስ ንግግር ኢሳይያስ ካሰፈረው ንግግር ጋር ሙሉ በሙሉ የሚገጥም ነው።

  3ኛ፦ " እግዚአብሔር እና መንፈሱ #ልከውኛል "  ልከውኛል የምለው ቃል እንደምታመለክተን ይሄ አካል የሚላክ ነው።  ከሶስቱ አካል በወንጌል መላካቸው የተጠቀሰው ደግሞ የኢየሱስ እና የመንፈስ ቅዱስ ነው። በዚህ ጥቅስ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ አንዱ ላኪ ነው ይሄ ማለት ያ የተላከው አካል ኢየሱስ ነው ማለት ነው።

   በሶስት ማሳያዎች ምዕራፉን የሚናገረው አካል ኢየሱስ መሆኑን አሳይተናል። በዚህም እስልምና በኢየሱስ ላይ ያለውን ምልከታ የዶግ አመድ እናደርገዋለን ማለት ነው!

   #በሁለተኛነት የምንመለከተው ቤተ - እምነት የይሖዋ ምስክሮችን ይሆናል። በእነርሱ እምነት ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ሳይሆን ከእግዚአብሔር አብ ያነሰ አምላክ ነው ብለው የሚያምኑ ሲሆኑ ከዛም ባለፈ መላኩ ሚካኤል ነው ይላሉ።(ሎቱ ስብሐት)!

     ይህ የእምነታቸውን በሁለት ማሳያ እናፍርሰው፦

#1ኛ፦    በመፅሐፍ ቅዱስ "አምላክ" የሚለው ቃል ከአንዱ እውነተኛ አምላክ ባለፈ ለፍጥረታትም ያገለገለ ሲሆን እነርሱን አምላክ ዘበፀጋ እንላቸዋለን በፀጋ አምላክ ከሆኑት ውጭ ለጣኦታትም መጠሪያ ያገለግላል ። በብሉይ እኒህ አምላክ ዘበፀጋ የሚባሉትን "አምላክ" ለማለት የገባው ቃል  "Elohim" ሲሆን ይሄ ለእግዚአብሔርም አገልግሏል። ይሄ የሚያሳየን እግዚአብሔር ለፍጥረቱ አምላክ የመባል ማዕረግን እንደሚሰጥ ነው። ግን እግዚአብሔር ለፍጥረቱ የማያጋራው የቃሉም ትርጉም እውነተኛውን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን ብቻ የሚያመለከት መጠሪያ አለ። "Yehôvâh" የሚለው መጠሪያ ለአንዱ እና ለእውነተኛው አምላክ ብቻ የሚያገለግል ሲሆን በዚህ ስም የትኛውም አምላክ ዘበፀጋ ወይንም ጣኦታት አልተጠሩበትንም። ይሄ ማለት በዚህ ስም የሚጠራው እግዚአብሔር እና እግዚአብሔር ብቻ ነው ማለት ነው።

     መልካም! ይሄንን ከተገነዘብን ወደ ምዕራፉ እንመለስ። ምዕራፉን የሚናገረው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ከላይ አስረግጠናል። ይህን ይዘን ቁጥር 17ን እንመልከት፦

     “ታዳጊህ፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ #አምላክህ #እግዚአብሔር #ነኝ።” ኢሳይያስ 48፥17

   በዚህ በቁ17 ላይ " እግዚአብሔር " በሚል የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል " Yehôvâh" ነው። ይሄንን መጠሪያ ደግሞ ከአንዱ እና እውነተኛው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ውጭ አያገለግልም። ይሄ ማለት ኢየሱስ እውነተኛው የእስራኤል አምላክ እንጂ ከእግዚአብሔር ያነሰ ፍጡር አምላክ ወይም በፀጋ አምላክ የተባለ አይደለም ማለት ነው። 


 #2ኛ፦ የይሖዋ ምስክሮች ኢየሱስ አስቀድሞ በሰማይ የተፈጠረ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው።ግን ኢየሱስ ፍጡር የሆነ አምላክ ከሆነ ከላይ ከጠቀስናቸው የአምላክ ባህሪያት ውስጥ አንዱ የሆነውን " ፊተኛውና ኋለኛው " መሆንን ይፃረራል ። ምክንያቱም ፍጡር የሆነ አካል የሆነ መነሻ ሰዓት ያለው ሲሆን  "ፊተኛው" መሆን አይችልም ማለት ነው። ይሄ ደግሞ ከዚች ከጥቅስ ብቻ ያይደለ  ከሙሉ ከመፅሀፍ ቅዱስ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ይፈርሳል ማለት ነው።


 በሶስተኛነት  የምናየው ቤተ - እምነት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን (onlyJesus)ሲሆን እንደእነርሱ እምነት እና ምልከታ ኢየሱስ እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው ባይ ናቸው። ይሄ አስተምህሮ በተነሳንበት ጥቅስ በኢሳ 48:16ስንመለከተው ፍፁም ስህተት መሆኑን እንረዳለን። ለዚህ ብዙም መናገር አያስፈልገውም ምክንያቱም በመጀመሪያ መፅሐፍ ቅዱስ የሥላሴ አስተምህሮን እንደሚፈቅድ ስናይ ይሄንንም በተዘዋዋሪ አይተነዋል። በዛው ላይ ሶስት ሙሉ መለኮታዊ ክብር ያላቸው አካላት መኖራቸውን አይተናል ያንን ስናይ ኢየሱስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ መሆኑንም አይተናል። ስለዚህ ብዙ ሳናትት የonly Jesus እምነች ተከታዮች አስተምህሮ ስህተት መሆኑን እንረዳለን ማለት ነው።


      02/07/2012 ተጻፈ 


          ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

         ወለወላዲቱ ድንግል!

         ወለመስቀሉ ክቡር!

          ይቆየን!!!


በቴሌግራም ያግኙን

ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

Comments

Popular posts from this blog

ዕቅበተ እምነት

ወላዲተ አምላክ

መልስ ለወሒድ ዑመር