ክፍ. ፭ የኢየሰስ አምላክነት ከአድስ ኪዳን(ክፍል ፭ ሐዋ. 20:28)
ክፍ. የኢየሰስ አምላክነት ከአድስ ኪዳን(ክፍል ፭ ሐዋ. 20:28)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ : በወልድ : በመንፈስ ቅዱስ ስም!
✝ገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች *የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት በአዲስ ኪዳን* በሚል መርሀግብር የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት እና ተቃዋሚዎች የሚያነሱት ጥያቄዎች ለመመለስ እየሞከርን ነው።(ለቀደመው ክፍል ፬[ የዮሐንስ 20:27 ]
ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የምንመለከተው፦
"... προσέχετε ἑαυτοῖς καὶ παντὶ τῷ ποιμνίῳ, ἐν ᾧ ὑμᾶς τὸ Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ἔθετο ἐπισκόπους, ποιμαίνειν τὴν ἐκκλησίαν τοῦ Θεοῦ, ἣν περιεποιήσατο διὰ τοῦ αἵματος τοῦ ἰδίου."
"...በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ..."(የሐዋርያት ሥራ 20:28)
በሚለው ቃል ተነስተን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የምንመሰክር ይሆናል።
የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት ከሚያስተምሩን የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል አንዱ የሀዋርያት ስራ 20/28 ነው። ደሙን አፍስሶ ቤተ ክርስቲያንን የዋጃት እግዚአብሔር እንደሆነ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ የሚያስተምር የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ነው።
በዚህ የሀዋርያት ስራ አንቀጽ ላይ ሀዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከኤፌሶን ለመጡ ጳጳሳት እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በገዛ ደሙ እንደዋጃት እና ይችንም ቤተ ክርስቲያን ይጠብቋት ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ እደተሾሙ ይናገራል።(ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሶስት ትርጉሞች ውስጥ አንዱ በክርስቶስ ያመኑ ክርስቲያኖች ስብስብን እንሚያመለክት እሙን ነው። በአውዱም የሚናገረው ስለዚሁ ነው።) በመፅሀፍ ቅዱስም እንደምንመለከተው ይችው ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር እንደሆነች በብዙ ቦታዎች ላይ ተጠቅሷል፦
"...ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን..."(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:32[በተጨማሪ 1 ቆሮ. 1:2፤ 10:32፤ 11:22፤ 15:9፣ 2 ቆሮ 1:1፣ ገላትያ 1:13 ]
ቅዱስ ጳውሎስም ይህም የቤተ ክርስቲያን ባለቤት ቤተ ክርስቲያንን ዋጅቶ የራሱ እንዳደረጋትም ይነግረናል።
በመጀመሪያ መዋጀት ምንድነው?
መዋጀት ምን ማለት እንደሆነ በይበልጥ በዚህ ንባብ ላይ የገባውን የግሪክ ቃል περιεποιήσατο (periepoiēsato) ትርጉም ስንመለከት ግልፅ ይሆንልናል። ትርጉሙም፦ purchase, make one's own; reserve for oneself ማለትም መግዛት፣ የራስ ማድረግ፣ ለራስ አድርጎ መያዝ ማለት ነው።
መዋጀት ማለት የራስ ማድረግ እስከሆነ ድረስና ይች ቤተ ክርስቲያንም የእግዚአብሔር ናትና ለራሱ የሚያደርጋት እራሱ እግዚአብሔር ነው።
ይህንም የሚያመለክተን መዋጀትን ለማመልከት የገባው ግስ *አመልካች ግስ*(indicative verb) ስለሆነ ነው።
Verb - Aorist #Indicative verb ነው
በቋንቋው ስንመለከትም አመልካች ግስ ካለ ከዚያ በፊት የድርጊቱ ፈፃሚ (doer of the action) ➞Subject(ባለቤት) አለ ማለት ነው። በሐዋርያት 20:28ም ስንመለከት አመልካች ግስ ከሆነው ከπεριποιέω (peripoieó) በፊት የድርጊቱ ፈፃሚ ተጠቅሷል
▻ #Θεοῦ, ἣν #περιεποιήσατο ◅
እርሱም 👉θεου(ቴዎስ) ወይም እግዚአብሔር የሚለው ነው። ስለዚህም በደሙ የዋጃት እራሱ የቤተ ክርስቲያን ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ነው። በዚህም አንቀፅ ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የዋጃት እግዚአብሔር መሆኑን ሲነግረን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ ይመሰክርልናል። ምክንያቱም ደግሞ በደሙ የዋጃት ከሶስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ተገልጦ ነውና።
ይህም ሆኖ ግን ጥያቄዎች ይሰነዘራሉ።
እነሱም፦
❓❶፦ በግሪኩ #τοῦ_αἵματος_τοῦ_ἰδίου የሚለው ሀረግ መተርጎም ያለበት *በገዛ ልጁ ደም* ተብሎ እንጅ *በገዛ ደሙ* ተብሎ አይደለም ስለዚህም
ደሙ የእግዚአብሔር ሳይሆን የልጁ ነው* የሚል ነው።
በመጀመሪያ ይህ ሙግት የሚመነጨው በግሪኩ #ἰδίου(ኢድዩ) ተብላ የተቀመጠችው ቃል ገላጭ/adjective ናትና ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግለፅ የመጣች ናት ስለዚህም ▻በገዛ *ልጁ* ደም◅ተብሎ መተርጎም አለበት የሚል ነው።
ይህን ግን ፈፅሞ የተሳሳተ ሙግት ነው ምክንያቱም
1▻ #τοῦ_αἵματος_τοῦ_ἰδίου (ተው ሄማቶስ ተው ኢድዩ) የሚለው ሐረግ ቃል በቃል ስንተረጉመው በደሙ በእርሱ በራሱ ተብሎ ይተረጎማል። ከላይ እንደተነጋገርንው ἰδίου የሚለው ቃል ገላጭ ቅፅል ሲሆን የሚቀጸለውም ἵματος በሚለው ስም ነው። በግሪክ ቋንቋ ሰወሰው ደግሞ ▻article+noun+article+adjective ማለትም
▻τοῦ + αἵματος + τοῦ + ἰδίου አይነት አወቃቀር
የተለመደ ነው።( daniel Wallace, Greek Grammar Beyond the Basics, 306-307. ) ማሳያውችንም፦
በዚሁ በ20:28 ላይ ይህንው ፎርም ይዞ እናገኘዋለን፦
τὸ Πνεῦμα τὸ Ἅγιον የተቀመጠበት አወቃቀር ከላይ የጠቀስንው አይነት (article+noun+article+adjective) ሲሆን ስም ከቅፅል ቡሃላ ከመጣች የምትገልጠው ሌላ አካልን ወይም በውስጥ አዋቂነት *ልጁን* ነው የሚለው ሙግት የተሳሳተ ነው።
ስለዚህም ወደ ተነሳንበት ስንመለስ #ἰδίου(ኢድዮ) የምትለው ቅፅል ሌላ ስም/noun ልትገልፅ አትችልም ምክንያቱም ደግሞ በዚሁ ቦታ ላይ የሰዋሰው አወቃቀሩን የተከተለ የተቀፀለችበት ስም(ደሙ የሚለው) ስላለ ነው።
ስለዚህም ሲተረጎም *በገዛ ደሙ* ተብሎ ነው።
2▻ ከዚህ በታች በምንመለከተው ክፍል መሰረት
ἰδίου *ደሙን* ስለምትገልፅ ነው።
"... διo καὶ Ἰησοῦς ,ἵνα ἁγιάσῃ διὰ #τοῦ_ἰδίου_αἵματος τὸν λαόν ,ἔξω τῆς πύλης ἔπαθεν.
"... ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ።"➞✝(ወደ ዕብራውያን 13:12)
እንደተቃዋሚዎች ከሆነ በዚህም ቦታ * በኢየሱስ ... በገዛ *ልጁ* ደም ተብሎ መተርጎም ነበረበት? በፍፁም!
ነገር ግን በዚህ ክፍል እየተነገረ ያለው *ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መቀበል* በደሙም ህዝቡን መቀደሱን
የአረፍተ ነገሩ ባለቤት(subject) ኢየሱስ ሲሆን በገዛ ደሙ የመቀደሱ ተግባር የኢየሱስ ነው ማለት ነው።
በተመሳሳይም በሐዋርያት 20:28 ስሙ የተጠቀሰው የቤተ ክርስቲያን ባለንብረት እግዚአብሔር ነው። የዋጃትም(የራሱ ያደረጋትም) በራሱ ደም ነው።
ስለዚህም *በገዛ ደሙ* ተብሎ መተርጎሙ ምንም አይነት ስህተት የለበትም።
❓❷፦ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፦(ዮሀንስ 4:24፣
መንፈስ ደግሞ ሥጋ እና አጥንት የለውም፦(ሉቃስ 24:39) ታዲያ ደሙ የእግዚአብሔር ወይስ የኢየሱስ?
ይህ የስህተት ሙግት የሚመጣው በመጀመሪያ በመፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር የተባለበትን ከፍል አለማንበብ ነው፦
"...በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ #ቃልም_እግዚአብሔር ነበረ።"(የዮሐንስ ወንጌል 1:1)
እንዲሁም በዮሀንስ 20:28 እግዚአብሔር፣ አምላክ በግሪኩ ቃል በሁለቱም ቦታዎች *ቴዎስ* ተብሏል።
[ https://t.me/ekbetemnet/437 ]
ስለ
ስለዚህም በዚህ ቦታ እግዚአብሔር የተባለው ኢየሱስ ነው።
ሁለተኛው ደግሞ አምላክ ሰው ሲሆን የሰውነት ባህርይ እና አካልን ገንዘቡ እንዳደረገ አለመመልከት ነው።
ከዚህ ቀደምም ስለ ተዋህዶ ምንነት በተነጋገርንበት መርሀግብር ላይ እግዚአብሔር ወልድ(ቃል) ስጋን ሲዋሃድ ያለመቀላቀል የስጋን ገንዘብ ገንዘቡ አድርጓል ስጋም የመለኮትን ባህርይ ገንዘቡ አድርጓል ብለን በሰፊው ተመልክተናል።
ለዚህም በትንቢት ላይ ሁሉ የሚያመልኩትና ዘለዓለማዊ ግዛት ያለው አምላክ የሰው ልጅ ተብሏል። ይህም የሆነበት ስጋን ተዋህዶ ከሰው ስለተወለደ ሰውነትን ገንዘቡ ስላደረገ ነው።
እንዲሁም ጌታ አምላክ ተሰቀለ ሞተም ተብሏል።
...(1ኛ ቆሮ. 2:8)"... ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።"(የዮሐንስ ራእይ 1:18)"... ሞቶ የነበረው ሕያውም የሆነው ፊተኛውና መጨረሻው እንዲህ ይላል።"(የዮሐንስ ራእይ 2:8)
ቅድመ ዓለም የነበረው እግዚአብሔር እንደሆነ የታወቀ ነው። የእግዚአብሔር አኗኗር ዘለዓለማዊ፤ ከ-ዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያለ ነው። ይህም አምላክ በራዕየ ዮሐንስ ላይ ሞቼ ነበርሁ፣ ሞቶ የነበረው ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ያለሁት እያለ ይናገራል። ስለዚህ ዘለዓለማዊ አምላክ ሞቻለሁኝ ተነስቻለሁም ካለን መለኮት በተዋሐዳው ሰውነት መሞቱ ልብ እንላለን።
ስለዚህም የሐዋርያት ስራ 20:28 የእግዚአብሔር ደም መባሉ ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ እና መለኮት የስጋን ባህሪና አካል ገንዘቡ እንዳደረገ የሚያስተምረን ነው።
✅ማጠቃለያ፦
በሐዋርያት ስራ 20:28 ላይ የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤት በደሙ ዋጅቶ የራሱ እንዳደረጋት ያስተምረናል። የቤተ ክርስቲያን ባለቤትም ደሙን ያፈሰሰላትና የዋጃት እራሱ እግዚአብሔር ነው። ስለዚህም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር እንደሆነ ይህ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ማስረጃችን ይሆናል።
በቀጣይ ክፍ. ፮[
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
_______________________
ክፈል ስድስት [ ሮሜ 9:5 ]
ክፍል ሰባት [ ቆላስይስ 1:15 ]
ክፍል ስምንት [ ታላቁ አምላክ ]
_______________________
ለማንኛውም አስተያየት፦
[ ዐቃቢያነ እምነት ዘኦርቶዶክስ ]
https://t.me/akabianement
ለቴሌግራም ቻናላችን፦
[ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ]
https://t.me/ekbetemnet
Comments
Post a Comment