ክፍ. ፪ የኢየሰስ አምላክነት ከአድስ ኪዳን ( ዮሐንስ 8:58)
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!
ሰላመ ክርስቶስ ከእናንተ ጋር ይሁን ተወዳጆች እንደምን አላችሁ? ዛሬ ከባለፈው የቀጠለውን የኢየሱስን አምላክነት በአዲስ ኪዳን ዳሰሳችንን የምንቀጥል ይኾናል አብረን እንመልከት።
የቀደመውን ክፍል ፩ን ለማግኘት [ የዮሐንስ ወ. 1:1 ]
ዛሬ ለመመልከት የወደድነው መነሻ ጥቅሳችን፦
“ኢየሱስም፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው።”(ዮሐንስ 8፥58) የሚለውን ነው።
ከዚህ ጥቅስ በመነሳት ኢየሱስ አምላክ እንደሆነ መናገሩን እና ከዚህ ጥቅስ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥያቄዎችን ጌታ በፈቀደ መጠን እንመለከታለን።
ይህ የዮሐንስ 8:58 ጥቅስ ኢየሱስ በራሱ አንደበት አምላክ መሆኑን ከተናገረባቸው የአዲስ ኪዳን ጥቅሶች መካከል አንዱ ነው። ይህ ጥቅስ ስለ ሁለት ምክንያት ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ያሳየናል፦
➊ኛ፦ የኢየሱስን ዘላለማዊነት ያሳየናል
በዚህ በዮሐንስ 8:58 ላይ " እኔ አለሁ" በማለት የተተረጎመው የግሪክ ቃል " εγώ ειμι (ego eimi)" የሚለው ሲሆን የእንግሊዝኛ ትርጓሜው "I am" የሚል ነው ይህም በአማርኛው መፅሀፍ ቅዱስ "እኔ ነኝ" ተብሎ ቢተረጎም መልካም የነበረ ነው።
ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ የእርሱን እና የአብርሃምን ህልውና በንፅፅር በሚመስል ያቀርባል።
" አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ" በሚለው ሀረግ ውስጥ " ሳይወለድ " የሚለው ቃል "γίνομαι: gínomai" ሲሆን በመፅሀፍ ቅዱስ ያለውን ትርጓሜ ስንመለከት የ Greek - English lexico መፅሐፎች ይህንን ይናገራሉ፦
➊፦ ginomai : to come into existence- 'to be formed, to come to exist.' Panta di autou egeneto'everything came into existence through him' Jn 1.3; prin Abraam genesthai ego eimi'before Abraham came into existence, I existed' Jn 8:58.
( Louw-Nida, Greek-English Lexicon of the New Testament: Semantic Domains, p.158)
➋፦γίνομαι= to come in to existence ; to be created , exist by creation John 1:3, 10 ; Heb 11:3 ; James 3:9 ; to be born , produced , grew, Matt 21:29 ; John 8:58 ; et (Perschbacher, The New Analytical Greek Lexicon, p. 80)
ከዚህም "γίνομαι(ginomai)" ማለት ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት እንደሆነ እንረዳለን። ይህም በህልውና ይኖር ያልነበረ አብርሃም ወደ ህልውና መምጣቱን ያሳየናል።
" እኔ ነኝ" በሚለው ሀረግ ውስጥ "ነኝ" ተብላ የተተረጎመችው "εἰμί(eimi)" የምትለው ቃል ደግሞ ከላይ ባስቀመጥናቸው መፅሐፎች ውስጥ ይህንን የመሰለ ትርጉም እንዳላት ተፅፎ እናገኛለን፦
➊፦13.69 eimi: to exist, in an absolute sense- 'to be, to exist.' Pisteusai… hoti estin'must have faith … that (God) exists' He 11:6; pro tou tov kosmon eivai'before the world existed' Jn 17:5;( Louw-Nida, Greek-English Lexicon of the New Testament: Semantic Domains, p.157
)
➋፦ εἰμί= verb of existence, to be, to exist, John 1:1; 17:5; Matt 6:30; Luke 4:25, et al. (Perschbacher, The New Analytical Greek Lexicon, p.119)
ከእነዚህ መፍቻዎች በቀላሉ እንደምንረዳው "eimi" ማለት "መኖርን" የሚያመለክት ነው። ስለዚህም ኢየሱስ በቅድመ ተዋሕዶ ጊዜው በህልውና ይኖር የነበረ ዘላለማዊ አካል መሆኑን እንረዳለን። ዘላለማዊ የሆነ አካል ደግሞ እውነተኛው አምላክ ብቻ ነው ይህም ማለት ኢየሱስ እውነተኛ አምላክ ነው ማለት ነው።
ስለዚህ ጥቅስ የግሪክ ቋንቋ ሊቁ A.T Robson " word pictures in the new testament " በሚለው መፅሐፋቸው በቅፅ 5 ላይ ያሰፈሩትን ልጨምር፦
"before coming as to Abraham," "before Abraham came into existence or was born." I am (egô eimi). Undoubtedly here Jesus claims #eternal_existence_with_the_absolute_phrase_used_of_God. The contrast between genesthai (#entrance_into_existence_of_Abraham) and eimi (#timeless_being) is complete.
ከዚህ እንግዲህ አስተዋይ ልቦና ላለው ሰው የኢየሱስን ዘላለማዊነት በግልፅ መረዳት ቀላል ነው።
➋ኛ፦ በዚህ ጥቅስ የኢየሱስን አምላክነት እንዲናይ የሚያደርገን ሁለተኛው ነገር ኢየሱስ በንግግሩ እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ መናገሩ ነው። ለዛም ነው አይሁዶች ሊወግሩት የፈለጉት፦ “ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።” — ዮሐንስ 8፥59
ምኑ ላይ ነው እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ያስተካከለው? የሚለውን ስንመለከት ከላይኛው ምክንያት በተጨማሪ " እኔ ነኝ" ሲል በብሉይ ኪዳን ያህዌ ከተናገረው ጋር አንድ አድርጎ ነው። ለዚህም ሁለት ምሳሌዎችን እናንሳ ፦
#የመጀመሪያው ፦ የዘፀአት 3:14 የግሪክ ትርጓሜው ይህንን ይላል፦
" και είπεν ο θεός προς Μωυσήν #εγώ_ειμι ο ων και είπεν ούτως ερείς τοις υιοίς Ισραήλ ο ων απέσταλκέ με προς υμάς "
እዚህ ላይ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ለሙሴ " እኔ ነኝ" ያለው በግሪኩ "#εγώ_ειμι) የሚል ሲሆን ይህ ደግሞ ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ካለበት ጋር ስናነፃፅረው አንድ ነው። ይኽም ኢየሱስ አምላክነቱን እየተናገረ እንደሆነ ያሳየናል። አይሁዶችም " እኔ ነኝ" በማለቱ ለምን ሊወግሩት ፈለጉ የሚለውን መልስ ይፈታልናል አይሁዶች ሊወግሩት የፈለጉበት ምክንያት "እኔ ነኝ" ሲህ እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እያስተካከለ ነውና ነው ።
#ሁለተኛው፦ ኢየሱስ ከዚህ ከዮሐንስ 8:58 በተጨማሪ በሌሎች ምዕራፍ ላይ "እኔ ነኝ" ሲል እናገኘዋለን። ለምሳሌ፦ ዮሐ 4:26 ፣ 13:18-19 ላይ ኢየሱስ "እኔ ነኝ" በማለት ይናገራል እኒህን የኢየሱስን ንግግሮች በብሉይ ኪዳን በትንቢተ ኢሳይያስ ከሚገኙት ከእግዚአብሄር ንግግሮች ጋር እያንዳንዳቸውን እናነፃፅራቸው፦
ኢሳይያስ 52:6 "... ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ እነሆ፥ እኔ ነኝ። #εγώ_ειμι αυτός #ο_λαλών" <=> ዮሐ 4:26 " “ኢየሱስ፦ የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት። #εγώ_ειμι_ο_λαλών"
ኢሳ 43:10 "“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥.... #ίνα γνώτε και #πιστεύσητε
και συνήτε #ότι_εγώ_ειμι"<=> ዮሐ 13: 19 "“በሆነ ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ፥.... #ίνα όταν γένηται #πιστεύσητε_ότι_εγώ_ειμι"
እኒህ ሁለት ጥቅሶች በቀላሉ ኢየሱስ "እኔ ነኝ" ሲል በብሉይ የነበረውን የእግዚአብሔር ንግግር ለራሱ በማድረግ እንደሆነ እንረዳለን። ይኽም ኢየሱስ እግዚአብሔር መሆኑን ያሳየናል።
በ ዮሐንስ 8:58 ዙሪያ የሚነሱ የተቃውሞ ጥያቄዎች ሲፈተሹ ፦
➊ኛ ጥያቄ፦ " እኔ ነኝ" ማለት አምላክ የሚያደርግ ከሆነ ሙሴስ " እኔ ነኝ" ብሎ የለምን?
#መልስ፦ ተቃዋሚዎች ይህንን ጥያቄ ሲያነሱ የኛን እምነት የሰሙ አይመስልም። እኛ ኢየሱስ ዩሐንስ 8:58 ላይ እና በሌሎችም ቦታ ላይ "እኔ ነኝ" ማለቱ #ብቻ አምላክ ያደርገዋል ብለን አልተናገርንም ምክንያቱም "እኔ ነኝ" የሚለው ማንነትን ለይቶ ለመናገርም ይውላል እና ነው። የኢየሱስን አምላክነት ያሳያሉ የምንላቸው "እኔ"ዎች ግን ከማንነት መለየት በተለየ መልኩ አውዱ አምላክነቱን እየተናገረ ነው እንዲንል ያደርገናል። ለምሳሌ ይህንንኑ የተነሳንበትን ጥቅስ ብንመለከት ኢየሱስ " እኔ ነኝ" ሲል ልክ ሙሴ ወይንም አይነ ስውር የነበረው ሰው ባለበት ሀሳብ ሳይሆን እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን በሚያሳይ መልኩ ነው ምክንያቱም አውዱ ስለ ኢየሱስ ቅድምና በሚገባ ይናገራልና። ከዚህም በተጨማሪ ዮሐ 18 ላይ ስንመለከት ኢየሱስ " እኔ ነኝ" ባላቸው ጊዜ ወታደሮቹ ሰግደዋል ኢየሱስ የተናገረው ልክ እንደነ ሙሴ ባለው ንግግር ከሆነ ለምን ሰገዱ? ይህን ተቃዋሚዎች እንዲመልሱልን እንጠይቃለን
➋ኛ ጥያቄ፦ እሺ ስለ ኢየሱስ አምላክነት ነው የሚለውን እንቀበላችሁ እና አብርሃም ኢየሱስን የት ነው ያዬው?
መልስ፦ ከጅምሩ ጥቅሱን በደንብ አላነበቡትም። እስኪ እኛ እናንብበው፦ “አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፥ አየም ደስም አለው።”— ዮሐንስ 8፥56
ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለውስን የሆነች ጊዜ ነው ያችንም ሰዓት "ቀኔን" በማለት ገልጿታል። በዚህ ንግግሩ "ቀኔን" የተባለው ጊዜ ኢየሱስ በምድር ለመመላለሱ ወሳኙ ምክንያት የሆነው እንደሆነ እንረዳለን። ለኢየሱስ በምድር መመላለስ ዋና ምክንያት ምንድን ነበረ? የሚለውን ስንመለከት የቅዱሳን አባቶች ተስፋ ፣ የነብያት ትንቢት የሆነው የኢየሱስ ለእኛ ለሰው ልጆች ሲል ተላልፎ መሰጠትን ነው። ኢየሱስ "ቀኔ" ሲል የመስቀሉን ጊዜ እንደሆነ እንረዳለን። እና አብርሃም የኢየሱስን ለእኛ በደል ተላልፎ መሰጠት በየት አዬ? ስንል እግዚአብሄር የኢየሱስን ስቅለት በልጁ በይስሐቅ እና በበጉ መስሎ አሳይቶታል፦
¹¹ የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፦ አብርሃም አብርሃም አለው፤ እርሱም፦ እነሆኝ አለ።¹² እርሱም፦ በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ አንድ ልጅህን ለእኔ አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ።¹³ አብርሃምም ዓይኑን አነሣ፥ በኋላውም እነሆ አንድ በግ በዱር ውስጥ ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብርሃምም ሄደ በጉንም ወሰደው፥ በልጁም ፋንታ መሥዋዕት አድርጎ ሠዋው።(ዘፍጥረት 22:11-13)
ስለዚህም አብርሃም የኢየሱስ ስቅለት በእግዚአብሔር ጸጋ በምሳሌ ተመስሎለት ተመልክቷል።
➌ኛ የተቃውሞ ጥያቄ፦ " ኢየሱስ "እኔ አለሁ " ሲል ልክ ሐዋርያውም ሆነ ነብዩ ኤርምያስ እንዳለው በእግዚአብሔር ሀሳብ በተስፋ ደረጃ እንጂ በአካል አልነበረም።"
መልስ፦ ኢየሱስ በስጋ ከመገለጡ በፊት በአካል ይኖር እንደነበረ በባለፈው ክፍላችን አይተናል ይኽም አሁን በዚህ ጥቅስ ኢየሱስ ዘላለማዊ ነው ስንል የቀደመውን ሀሳባችንን የሚደግፍ ነው። ግን እኒህ ተቃዋሚዎች ስለዚህ አባባላቸው ምንም አይነት ጠንካራ ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም ምክንያቱም ειμι የምትለው ቃል በሀሳብ መኖርን የሚያመለክት ሳይሆን በህልውና መኖርን የሚያመለክት ነው። በሀሳብ ደረጃ የኖረን አካል ለማመልከት የዋለበት ቦታ ካለ እንዲያሳዩን በትህትና እንጠይቃቸዋለን። #በሀሳብ_ደረጃ_ይኖር_የነበረው_ወደ_ምድር_ወርዶ_የሚከውነው_ተግባር እንጂ እርሱ እራሱ ኢየሱስ አልነበረም።
በዚህ ፅሁፍ የዮሐንስ 8:58ን እውነታ ተመለከትን በቀጣይ ክፍል ሶስት [ የዮሐንስ ወ. 10:30 ] እንመለከታለን እስከዛው ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ክፍል ሶስት [ የዮሐንስ ወ. 10:30 ]
ክፍል አራት [ የዮሐንስ ወ. 20:28 ]
ክፍል አምስት [ የሐዋርያት ስራ 20:28 ]
ለማንኛውም አስተያየት፦
[ ዐቃቢያነ እምነት ዘኦርቶዶክስ ]
https://t.me/akabianement
ለቴሌግራም ቻናላችን፦
[ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ]
https://t.me/ekbetemnet
Comments
Post a Comment