ስቅለት ለምን

     አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡በመንፈስ ቅዱስ ስም!

   ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰቀለ የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው?አዎመጠየቅም አለበት። ወደሌላ ርዕስ ከመግባትም በፊት የስቅለት አላማ ግልፅ መሆን አለበት። 


    አዳም ከተፈጠረ በኋላ እግዚአብሔር አንዲትን ትዕዛዝ ለአዳም ሰጥቶት ነበረ። ትዕዛዙም፦

(ኦሪትዘፍጥረትምዕ.2:16-17)

16-እግዚአብሔርአምላክምሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው። ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ 17-ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና። 

ነገር ግን አዳም እግዚአብሔር ከሰጠው ትዕዛዝ ተላልፎ   ከዛፏ ቆርጦ በለስን በላ። (ኦሪትዘፍጥረትምዕ 3:3-10)➫ነገርግንበገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ እግዚአብሔር አለ። እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም። እባብም ለሴቲቱ አላት። ሞትን አትሞቱም፤

...6፤ሴቲቱምዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ #ከፍሬውም_ወሰደችና_በላች፤ #ለባልዋም_ደግሞ_ሰጠችው_እርሱም_ከእርስዋ_ጋር_በላ።

አዳምና ሄዋን አትብሉ የሞትን ሞት ትሞታላችሁ ብሎ እግዚአብሔር ቢነግራቸውም ነገር ግን እነርሱ የዲያቢሎስን ምክር በመስማት በለሷን በሉ ሞቱም። 

በዚህም ምክንያት ከገነት ተባረሩ፦ (ኦሪትዘፍጥረትምዕ.3)--23፤ስለዚህእግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ።24፤ አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ። 


     "አንዳንድ ሙስሊሞች እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ከሆነ አዳም በበደለ ጊዜ ለምን ይቅር አላለውም?"ብለው ይጠይቃሉ ፦ እነርሱ ግን ያላስተዋሉት አንድ ነገር አለ። እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ እንደሆነ ሁሉ የፍትሕም አምላክ ነው። እግዚአብሔር ቃሉ የፀና ነውና አዳምን ትእዛዜን በተላለፍክ ጊዜ ሞትን ትሞታለህ ባለው መሰረት አዳም ሞተ። ሞትን ትሞታለህ ብሎት ግን አዳም ሳይሞት ቢቀር ኖሮ እግዚአብሔር የፍትህ አምላክ መሆኑ ይቀርና ፍርዱ ከፍትህ የራቀ ይሆናል። የመስቀሉን ነገር ላስተዋለው ሰው  በእውነት የእግዚአብሔር ፍትሕና ፍቅር በአንድነት የተገለፀበት ነው።

       ዮሀንስ ሐዋርያ ይህንን ብሏል፦


    “በዚህ #የእግዚአብሔር #ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።”  — 1ኛ ዮሐንስ 4፥9


      የመስቀሉ ስራ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበት መሆኑን ከዚህ እንረዳለን።

አዳምና ሄዋን እኛም ያጣነው ነገር ምንድነው?


⓵-ከእግዚአብሔር መለየት፦ እግዚአብሔር ለአዳም በለሷን በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ ብሎት ነበረ(...ከእርሱበበላህቀን ሞትን ትሞታለህና። ዘፍ.2:17)ነገርግን አዳም በበላት እለት የሞተው ሞት ከእግዚአብሔር መለየቱ ነው ምክንያቱም እርሱ ስጋው ከነፍሱ የተለየው/የሞተው በ937 አመቱ ነበረ።

2-የስጋና የነፍስ መለየት፦ ይህ ሞት ስጋ ከነፍስ መለየት ነው። የመጀመሪያው ስጋው ከነፍሱ የተለየው ሰው አቤል ነው።("በሜዳምሳሉቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ #ገደለውም። "

(ኦሪትዘፍጥረት4:8፤)

:

ስለዚህምየሰውልጅ በሙሉ ከእግዚአብሔር ተለየ።ይህም ቅጣት በአዳም በኩል ለሰው ልጆች ሁሉ ውድቀት ሆነ 

(1ኛወደቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ.15)_21፤ሞትበሰውበኩል ስለ መጣ...ሁሉበአዳምእንደሚሞቱ...


⓶➝ፀጋችንተገፏል፦

 ሰው ሲፈጠር በእግዚአብሄር መልክና አምሳል ነው የተፈጠረው👉"26፤ እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር።(ኦሪትዘፍጥረት1:26)የእግዚአብሔርመልክና ምሳሌ ማለት ቅድስና ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ዘለአለማዊነት እና የመሳሰሉት ናቸው። ስለዚህም በገነት የብርሃንን ልብስ ለብሰው ይኖር የነበሩ ሲሆን ነገር ግን ሀጥያትን ከፈፀሙ እግዚአብሔርም ያዘዛቸውን በመተላለፋቸው ምክንያት ራቆታቸውን ቀርተው ነበረ።(ዘፍጥረት3:7)

ይህራቁታቸውንመቅረትም የጸጋቸው መገፈፍ ነበረ።

በመፅሀፍ ቅዱስ እንዲህ ተብሎ እንደተቀመጠ"ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች። "(መጽሐፈምሳሌ14:34)


⓷➝ልጅነትንማጣት፦

 አዳም ሲፈጠር እግዚአብሔር በውሃና በመንፈስ ቅዱስ አጥምቆ ልጁ አድርጎት ነበረ(ዘፍጥረት1:2፤2:7)ነገርግን በለስን ከበላ ቡሃላ ይህን ልጅነትን አጥቶ ነበረ።(ዮሐንስ3:3)


⓸➝ከገነትመባረር:-እግዚአብሔርአዳምን ከፈጠረው ቡሃላ በኤደን ገነት አስቀምጦት ነበረ👉 "8፤ እግዚአብሔር አምላክም በምሥራቅ በዔድን ገነትን ተከለ የፈጠረውንም ሰው ከዚያው አኖረው።"(ኦሪትዘፍጥረት2:8)ነገርግንአዳም ሃጥያትን ባደረገ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ከገነት አስወጣው👉"ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ።"(ኦሪትዘፍጥረት3:23፤)

ስለዚህምአዳምንካስወጣው ቡሃላ ገነትን የሚጠብቁ የእሳት ነበልባል ሰይፍን አስቀምጠ። ስለዚህ አዳም መልሶም አይገባም።

ይህ ሁሉ ቅጣት በአዳም ልጆች ሁሉ ተላልፏልና ነብዩ ኢሳያስ እንዲህ "...#ሁላችን_እንደ_ርኩስ_ሰው_ሆነናል፥ #ጽድቃችንም_ሁሉ_እንደ_መርገም_ጨርቅ_ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። "(ትንቢተኢሳይያስ64:6)

ማንምሰው ፅድቅን ቢሰራ አይቆጠርለትም እንደመርገም ጨርቅ ይሆንበታልንጅ የመርገም ጨርቅ ማለት የደም ጨርቅ ሲሆን ምን ቢታጠብ አይጠራም ይህም የሆነበት ምክንያት በአዳም ምክንያት የመጣብን ቅጣት ነበረ ስለዚህም ፅድቃችን እንደ መርግም ጨርቅ ሆነ።

    እኒህ ያጣናቸውን ነገሮች ግን በመስቀሉ በተሰራው የድህነት ስራ አግኝተናቸዋል ምክንያቱም ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ቅጣት በሙሉ በእርሱ ላይ አድርጎ ስለተቀጣልንና እኛ መክፈል የነበረብንን ዋጋ ስለከፈለልን ነው በትንቢትም እንዲህ ተቀምጧል፦

(ትንቢተኢሳይያስ 53:-

4፤በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። 5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።6፤ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን መተላለፍ የእኛን ደዌ ይዞ በመስቀል ላይ ስለ እኛ ቤዛ ሆኖ በመቁሰሉ ምክንያት ያ ቅጣታችን ሁሉ በእርሱ በክርስቶስ ተዎግዶልናል። ያጣነውም ሁሉ ተመልሶልናል። ከእነርሱም መካከል፦


➊=> እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሆነው ከውልደቱ ጀምሮ ነው። 

      “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦👉 #እግዚአብሔር #ከእኛ #ጋር የሚል ነው።”— ማቴዎስ 1፥23

      በፍፁምነት ግን እኛን ከእግዚአብሔር ጋር የለያየን የጥል ግድግዳ የፈረሰው በመስቀሉ ነው፦

      “ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።”— ኤፌሶን 2፥16

➋=> ፀጋችን ከአዳም ጀምሮ ተገፎ ነበር ለዛም ነው ፀጋን የተመላ በብሉይ ማንም ያልነበረው። በመስቀሉ ግን ፀጋን አግኝተናል፦

    ሮሜ 3

"...²³ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤²⁴ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።

➌=> እግዚአብሔርን  አባት ብሎ የመጥራት ፀጋን ኢየሱስ አድሎናል፦

       “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤”— ዮሐንስ 1፥12


➍=>  ገነትን ያህል እርስት በበደላችን ምክንያት ያጣን ቢሆንም በእርሱ ቸርነትና በርህራሄ ግን ከአዳም ጀምሮ ለነበሩ የሰው ልጆች በሲኦል ሂዶ ወንጌልን ሰበከላቸው ወደገነትም አገባቸው፦ 

       “በእርሱም ደግሞ ሄዶ በወኅኒ ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤”— 1ኛ ጴጥሮስ 3፥19

በቀጣይ ክፍል ስለ ስቅለት የሚነሱ ጥያቄዎችን እንመልሰለን!


      14/07/201 ተጻፈ

       ወስብሐት ለእግዚአብሔር!


       ለማንኛውም አስተያየት፦
[ ዐቃቢያነ እምነት ዘኦርቶዶክስ ]

ለቴሌግራም ቻናላችን፦
[ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ]


Comments

Popular posts from this blog

ዕቅበተ እምነት

ወላዲተ አምላክ

መልስ ለወሒድ ዑመር