ሊሞት ከመጣ ለምን ከአይሁድ ሸሸ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ኢየሱስክርስቶስ ስለእኛ ሊሞት ከመጣ ለምን ከአይሁድ ሸሸ?
"...ከዚህም በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር በይሁዳ ሊመላለስ አይወድም ነበርና በገሊላ ይመላለስ ነበር።"(የዮሐንስወንጌል 7:1)
"...ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወራቸው ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።"(የዮሐንስወንጌል 8:59)
(የማርቆስወንጌል ምዕ.8)
"...ወደ ቤቱም ሰደደውና። ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው።...30፤ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛ ሊሞት ከመጣ ለምን ከአይሁድ ሸሸ?
ሙስሊም ወገኖች እንዲሁም ሌሎች ተቀዋሚዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ላለመቀበል ብዙ ይጥራሉ። ለእነርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ በአንደበቱ #እሰቀላለሁ_እሞታለሁም ያለው ጉዳያቸው አይደለም። ይልቁንም መሰናከያን ጥያቄ ያነሳሉ፦ """እንደነገራችሁን ኢየሱስ ክርስቶስ ሊሰቀል ከመጣ ለምን አይሁድ ሊገድሉት ሲነሱ ሸሻቸው፣ ለምን ተደበቃቸው?""የሚል ነው።
በእርግጥ ይህ ጥያቄ የመነጨው እግዚአብሔር ለሚሰራው ጉዳይ ሁሉን በጊዜው እንደሚሰራ አለማወቅ ነው። ይህችን አለምና በውስጧ ያሉትን ሲሰራ ሰባት ቀን የፈጀበት በአንድ ቀን በአንድ ሰአት በአንድ ሰከንድ ...መስራት አቅቶት አይደለም። ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስ እንዳለው """...ነገርንሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው..."(መጽሐፈመክብብ 3:11)ሚስጥሩ ይህ ነው። እግዚአብሔር የሚሰራውን ነገር ሁሉ በጊዜና በሰአት በ Chronological order አስይዞ ነው የሚሰራው። ጠቢቡ እንዲህ እንዳለን፦
"...ለሁሉ,ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። "(መጽሐፈመክብብ 3:1)...ኢየሱስክርስቶስ ተልዕኮውን በጊዜ እንደሚሰራ የምናውቀው የዘመኑ ፍፃሜ ሲደርስ መወለዱ ነው፦ "...ነገር ግን #የዘመኑ_ፍጻሜ_በደረሰ_ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤"
(ወደገላትያ ሰዎች 4:4)ኢየሱስ ክርስቶስ የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እንደመጣሁ ሁሉ ሊሰቀል የሚገባውም በጊዜው ነበረ ምክንያቱም ለሁሉም ጊዜ አለውና። ለዚህም ጌታችን ከኢየሩሳሌም ውጭ የመንግስቱን ወንጌል ከሰበከ ቡሃላ ሊሰቀል ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱ ሁሉም በጊዜው እንደሚፈፀም ለማጠየቅ ነው፦
(የማቴዎስወንጌል ምዕ.20:18-19)
"... እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፥ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፥ .. ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፥ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል አላቸው።
ሌላው ጉዳይ ነፍሱን በራሱ ፈቃድ ይሰጣል እንጅ ተገዶ ስለማይሰቀል ነው። ከላይ ያለው አመክንዮ እንዳለ ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ጊዜው በደረሰ ጊዜ የሚሰጠዉ በፈቃዱ እንጅ አይሁድ አስገድደውት አልነበረም፦ "... እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።"(የዮሐንስወንጌል 10:18)
ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድ ሊገድሉት ሲሉ የሸሸው ሁሉን በጊዜው ለመፈፀምና በአይሁድ ተገዶ ሳይሆን የሚሞተው በፈቃዱ ስለሆነ ብቻ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ቀጣይ ክፍል [ ይች ጽዋ ከእኔ ትለፍ]
______________✝
ለማንኛውም አስተያየት፦
ለቴሌግራም ቻናላችን፦
Comments
Post a Comment