ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!
"ይህች ፅዋ(ሞት)ከእኔ ትለፍ ብሎ ለምኗል አምላክም ልመናውን ሰምቷል ስለዚህ እየሱስ ክርስቶስ ላለመሰቀሉ ማስረጃ አይሆንምን?"
➞በጌቴሰማኒ የኢየሱስ ክርሰቶስ ፀሎት👇
"...ጥቂትምወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ። አባቴ፥ ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን አለ።"(የማቴዎስወንጌል 26:39)
"...ከእነርሱም የድንጋይ ውርወራ የሚያህል ራቀ፥ ተንበርክኮም። 42፤ አባት ሆይ ብትፈቅድ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ አይሁን የአንተ እንጂ እያለ ይጸልይ ነበር።(የሉቃስወንጌል ምዕ.22:41-42)
➞ልመናውንሰምቷል ብለው የሚያነሱት ቃል👇
✟➫"...ድንጋዩንም አነሡት። ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ። ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።(የዮሐንስወንጌል ምዕ.11:41-42)
✟➫"...እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤"(ወደዕብራውያን 5:7)
የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት ላለመቀበል ሙስሊም ወገኖቻችን እንዲሁም ሌሎች ተቃዋሚዎች ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል ከላይ በተቀመጠው የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ተነስተው ""ይህች ፅዋ(ሞት)ከእኔ ትለፍ ብሎ ለምኗል አምላክም ልመናውን ሰምቷል ስለዚህ እየሱስ ክርስቶስ ላለመሰቀሉ ማስረጃ አይሆንምን?""ብለው የሚጠይቁት ነው።
ከዚህ ቀደም በነበረው ፖስት እንደተነጋገርንው ኢየሱስ ክርስቶስ በእራሱ አንደበት ወደ ኢየሩሳሌም ከመግባቱ በፊት የመጣበትን አላማ ሲናገር በመስቀል ላይ ለእኛ ቤዛ ሆኖ ሞቶ በሶስተኛው ቀን ቡሃላ ተነስቶ እንደሚያርግ መናገሩ የታወቀ ነው። ስለዚህ ከላይ ባለው ቃል ተነስተን የኢየሱስ ክርስቶስን ስቅለት ማስተባበል በፍፁም የለየለት ክህደት ነው።
የምንባቡን ትርጉም እንደሚከተለው እንመልከተው፦
ማንም ክርስቲያን የማይክደው ሃቅ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴሴማኒ በአትክልት ቦታ መፀለዩን ነው። ፀሎቱም በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የታጀበ ነበረ ይህም በተዋሃደው ስጋ ገንዘቡ ባደረገው የስጋ ባህሪ ምክንያት ነው(መራብ፣መጠማት፣ መተኛት....እነዚህ ሁሉ በስጋው ወራት በተዋሃደው ስጋ የመጡ ናቸው)።ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ያን ፀሎት ያደረገው የመስቀል ሞት እጅግ አሰቃቂ ስለሆነ ፍፁም አምላክ ሳለም ፍፁም ሰው ስለሆነ ፍርሃት በሚስማማው በሰውነቱ ይህን ፀሎት ለአባቱ አቅርቧል።
ነገር ግን የፀለየውን ፀሎት ቆም ብሎ ላጤነው ሰው ስቅለቱንም የሚያጠናክር ቃል አለው። ➞"...ብትፈቅድይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን #የእኔ_ፈቃድ_አይሁን_የአንተ_እንጂ_እያለ_ይጸልይ_ነበር።"(የሉቃስወንጌል 22:42)___ግሩምነው!...ኢየሱስክርስቶስ ይህች ፅዋ ከእኔ ትለፍ ማለቱንብቻ ነውንዴ ጠያቂዎች ያነበቡት?!ፀሎቱን የዘጋው
➞ #የእኔ_ፈቃድ_አይሁን_የአንተ_እንጂ_እያለ_ይጸልይ_ነበር። በማለት ነው። መፅሀፍ ቅዱስ አነበብን ለሚሉን ወገኖች ጥያቄ እንጠይቃቸው ➞የአብ ፈቃድ ምንድነው?መልሱ
"....ልጅንምአይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ።"(የዮሐንስወንጌል 6:40)
"...ሙሴምበምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።"
(የዮሐንስወንጌል 3:14-15)
✅የአባቱፈቃድ በልጁ አምኖ የዘለአለም ህይወትን እንዲያገኙ ነው። የዘለአለም ህይወትን ደግሞ እንዲቀዳጁ ልጁ መሰቀል አለበት። የአብ ፈቃድ ይህ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎቱን ያጠናቀቀው ""ከእርሱ ይልቅ የአባቱ ፈቃድ እንዲፈፀም ስለሆነ፤ የአባቱም ፈቃድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሰቀልና በእርሱ የሚያምን የዘለአለም ህይወትን እንዲያገኝም ከሆነ የአባቱ ፈቃድ በፀሎቱ አማክኝነት ተፈፅሟል።"" ስለዚህም አፋችንን ሞልተን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት ተሰምቷል ስንልም የአብ ፈቃድ ለመፈፀሙም ምስክር ነን እርሱም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀል ነው።
____
ሌላው ጉዳይ በዕብራውያን 5:7ላይ ፀሎትና ምልጃው ተሰማለት የተባለውን ይዘው ኢየሱስ ክርስቶስ አልተሰቀለም በማለት ይሞግታሉ። ነገር ግን ሙሉውን የዕብራውያንን የወንጌል መልዕክት ቢመለከቱት ስለኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀል አጥብቆ ይናገራል። ለአብነት ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፦
"...ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ #ስለ_ሰው_ሁሉ_ሞትን_ይቀምስ_ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን።
ብዙ_ልጆችን_ወደ_ክብር_ሲያመጣ_የመዳናቸውን_ራስ_በመከራ_ይፈጽም_ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና።(ወደዕብራውያን ምዕ.2:9-10)
_"...እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ #እርሱ_ደግሞ_በሞት_ላይ_ሥልጣን_ያለውን_በሞት_እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።"(ወደዕብራውያን 2:14-15)
_"...እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።"(ወደዕብራውያን 12:1-2)
_"20፤በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥"(ወደዕብራውያን 13:20)
እነዚህንብቻ ለአብነት ጠቀስኩኝንጅ ሙሉውን የዕብራውያን የወንጌል መልዕክት ብታነቡት በኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀል ወይም የመስቀል ዋጋው ለድህነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ለዕብራውያን የተገለፀበት መልዕክት ነው።
ወደ ቀደመው ነገር እንመለስና ""ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት"" ማለት ምን ማለት ነው?
ከላይእንደተመለከትንው ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን ተቀብሏል፣ በመስቀል ተሰቅሏል፣ ሞቷል፣ ከሞትም ድኗል(ሞትንድል አድርጎ ተነስቷል)።
ፀሎቱየተሰማለት ከመሰቀል በመዳን ሳይሆን ከሞተ ቡሃላ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ በትንሳኤው ነው። ሞትን ድል አድርጎ በመነሳቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በዛው ሞት ስላልቀረ ከሞት ድኗል።
በዚህ ዙሪያ ያለን መልስ ይህ ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ቀጣይ ክፍል [ ትፈልጉኛላችሁ አታገኝኝም ]
______________✝
ለማንኛውም አስተያየት፦
[ ዐቃቢያነ እምነት ዘኦርቶዶክስ ]
ለቴሌግራም ቻናላችን፦
[ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ]
Comments
Post a Comment