የኡስታዙ ውዝግብ
የእግዚአብሄር ፍጥረት የመጀመሪያው ማነው? ጉማሬ? ሰማይናምድር? ወይስ ኢየሱስ? ብሎ ድንክርክር ላለው ኡስታዝ ወሒድ የተሰጠ መልስ!
ይህ ሰው እራሱን የግሪክ እና የእብራይስጥ አስተማሪ አድርጎ የሾመ ሰው ሲሆን ይህን ተገን አድርጎ ሙግቶችን በእነዚህ ቋንቋዎች የሚያቀርብ ሰው ነው። ለጠየቀውን ጥያቄ ከዚህ በታች የእርሱንም እውቀት እየገመገምን እንመልከተው፦
ጥያቄውም፦
የእግዚአብሄር ፍጥረት የመጀመሪያው ማነው? ጉማሬ? ሰማይናምድር? ወይስ ኢየሱስ?
በመጀመሪያ ይህን ጥያቄ ለምን እንደተነሳ ከታች የምናየው ቢሆንም ጥያቄው የተነሳው መፅሀፍ ቅዱስን ጠንቅቆ ካለመረዳትና ከድርቅና የሆነ እንጅ እግዚአብሄር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን እንደፈጠረ በዘፍጥረት 1:1 ላይ በግልፅ "እግዚአብሔር መጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ" ተብሎ የተነገረ ሲሆን ጠያቂው ግን ይህን እንዳላዩ አልፎ በእሱ ሀሳብ መጀመሪያ ተፈጠሩ የሚላቸውን የመፅሀፍ ቅዱስን ቃል በማጣመም አስቀምጧል።
በመቀጠልም...
A-ጉማሬ፦ ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፤ መጽሐፈ ኢዮብ 40 : 15
እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው፤ መጽሐፈ ኢዮብ 40 : 19
He [is] the chief of the ways of God: he that made him can make his sword to approach [unto him]. Job 40 : 19
አውራ ተብሎ የተቀመጠው ቃል መጀመሪያ the first የዕብራይስጡ ደግሞ "ረሺት" ማለት ሲሆን ለሰማይና ምድር መጀመሪያነት ተጠቅሷል።]
መልሴ፦ በመጀመሪያ "רֵאשִׁ֤ית"(reshit) የምትለው ቃል የፍጥረትን መጀመሪያ ለመጥቀስ ብቻ የምትውል ናት የሚል ድምዳሜ በዕብራይስጥ የቋንቋ ህግ የለም አይኖርምም። እስኪ ከዚህ በመቀጠል የቃሏን ትርጉም እና አገባብ እንመልከት፦
• (reshít) רֵאשִׁ֤ית
the first in place, time, order or rank: - beginning, chief (-est), first (-fruits, part, time), principal thing.
መጀመሪያ ማለት ስትሆን ይህም ለቦታ ለስአት ለቅደም ተከተል እንዲሁም ለደረጃ፣ ለዋና ነገር ጥቅም ላይ ትውላለች።
፩-መጀመሪያ ለሰአት፦ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
ኦሪት ዘፍጥረት 1 : 1
📜... Be reshit 👈 bara Elohim et hashamayim ve'et ha'aretz.
በዚህ ቦታ ላይ እንደምንመለከተው እግዚአብሄር ከሁሉ በሰአት በጊዜ አስቀድሞ ሰማይንና ምድርን ስለፈጠረ በመጀመሪያ ፈጠረ ተባለ። ስለዚህም በዚህ ቦታ የጊዜ ቀዳሚነትን ለመጠቆም ጥቅም ላይ ውላለች።
፪~መጀመሪያ ለሀያልነት፦
አማሌቅንም አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ። አማሌቅ የአሕዛብ #አለቃ ነበረ።ኦሪት ዘኍልቍ 24 : 20
מְשָׁל֖וֹ וַיֹּאמַ֑ר #רֵאשִׁ֤ית גּוֹיִם֙ עֲמָלֵ֔ק
አለቃ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ reshit(רֵאשִׁ֤ית) መሆኑን ልብ ይበሉ።
አማሌቅ በሀያልነቷ ከአህዛብ ሁሉ የገነነች አህዛብን ቀጥቅጣ የምትገዛ ስለሆነች የአህዛብ አለቃ(רֵאשִׁ֤ית) ተባለች።
ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል ነገር ግን ለአስተዋይ ሰው ይች በቂ ናት።
እሽ እንግዲህ ይህን ሁሉ የ"רֵאשִׁ֤ית"ትርጉም ካየን እስኪ በመፅሀፈ ዕዮብ ያለው ቃል ምን ለማለት ተፈልጎ ነው የሚለውን እንመልከተው፦
15-ከአንተ ጋራ የሠራኹትን ጕማሬ፥እስኪ፥ተመልከት እንደ በሬ ሣር ይበላል።16-እንሆ፥ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው ኀይሉም በሆዱ ዥማት ውስጥ ነው።17-ዥራቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወዛውዛል የወርቹ ዥማት የተጐነጐነ ነው።18-አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው አካላቱ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው።19-ርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው።
እሽ መልካም እንግዲህ ጉማሬ ለምን መጀመሪያ ተባለ የሚለውን ለማወቅ ከአሁዱ እንመለከታለን
ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው
ኀይሉም በሆዱ ዥማት...
አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው
አካላቱ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው።
አንባቢ አስተውል!...ጉማሬ መጀመሪያ የተባለው በሀይሉ በብርታቱ በሰውነቱ ጥንካሬ ለመሆኑ ፍንትው ያለ ማስረጃ ከዛው ከአውዱ ተቀምጧል ስለዚህ መጀመሪያ የተባለበት ምክንያት ስንመለከት በመፈጠር አንፃር ሳይሆን በሀያልነቱ በጥንካሬነቱ ነው። ""reshit""የምትለው እንደ አገባቧ እንደምትለይ ተመልከቱልኝ።
በመቀጠልም ወሂድ እንዲህ ይላል፦
ሰማይና ምድር!
በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። ኦሪት ዘፍጥረት 1 : 1
መልስ፦
ይህን ቃል በመከተል የተለመደ የቋንቋ ትንታኔውን በማስከተል የመጀመሪያው የእግዚአብሔር ፍጥረት ሰማይና ምድር ናት ብሎ ተናግሯል፤ ለዚህም ምንም አጠያያቂ የለውም። ፈጠረ ስለሚልም የመጀመሪያ ፍጥረት ለመሆኗ አጠያያቂ አይደለም። ከላይ ተነተን አድርጌበታለሁና ተመልሰው ይመልከቱ።
ኢየሱስ
የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል።የዮሐንስ ራእይ 3 : 14
መልስ፦
እዚህ አንቀፅ ላይ ደግሞ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ነው ይለናል።
በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስጀፉ ከፈጀፈክር፥ የእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል።የዮሐንስ ራእይ 3 : 14
አዲስ ኪዳንን ስንመለከት ἀρχή (አርኬ) የሚለው ቃል የጊዜ መቅደምን ብቻ ሳይሆን ገዢነትን ወይንም ሥልጣንንም ያመለክታል፡፡
arché: beginning, origin
Original Word: ἀρχή, ῆς, ἡ
Definition: beginning, origin
Usage: (a) rule (kingly or magisterial), (b) plur: in a quasi-personal sense, almost: rulers, magistrates, (c) beginning.
ለምሳሌ ያህል ሉቃስ 20፡20
Καὶ παρατηρήσαντες ἀπέστειλαν ἐνκαθέτους ὑποκρινομένους ἑαυτοὺς δικαίους εἶναι, ἵνα ἐπιλάβωνται αὐτοῦ λόγου, ὥστε παραδοῦναι αὐτὸν τῇ #ἀρχῇ καὶ τῇ ἐξουσίᾳ τοῦ ἡγεμόνος
ሉቃስ 20:20 “ሲጠባበቁም ወደ ገዢ ግዛትና #ሥልጣን አሳልፈው እንዲሰጡት …” በሚለው ቃል ውስጥ “ሥልጣን” የሚለው “አርኬ” ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ 1ቆሮንቶስ 15፡24 ላይ “ሥልጣን” ተብሏል፡፡
εἶτα τὸ τέλος, ὅταν παραδιδοῖ τὴν βασιλείαν τῷ Θεῷ καὶ Πατρί, ὅταν καταργήσῃ πᾶσαν #ἀρχὴν καὶ πᾶσαν ἐξουσίαν καὶ δύναμιν
እንዲሁም በሌሎች ብዛት ባላቸው ቦታዎች ላይ ገዢ ስልጣን እየተባለ ተተርጉሟል።
ስለዚህም በዚሁ በራዕየ ዮሀንስ 3:14 ላይም የተጠቀሰው የኢየሱስን ገዢነት እና ከፍጥረት ሁሉ በፊት ቀድሞ መኖርን ለማመልከት እንጅ ፍጡር ነው እያለን አለመሆኑን ልብ በሉ።
በመጨረሻም ወሂድ የተጋጩ የመሰሉት የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች አለማንበቡንና የእሱን የእውቀት ውሱንነት የሚገልጡ ናቸው።
Comments
Post a Comment