ምስጢረ_ሥላሴ ክፍል ፫
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!
ለቀደሙት ክፍሎች፦
ባለፉት ሶስት ተከታታይ ፖስቶች ስለ ምስጢረ ሥላሴ ለምን ምስጢር ተባለ? ከሚለው ጀምረን በብሉይ ኪዳን ያሉ ማስረጃዎችንም ማቅረባችን ይታወሳል። ለዛሬ ደግሞ አምላክ እንደወደደና እንደፈቀደ በአድስ ኪዳን ያሉ ማስረጃዎችን እንመለከታለን።
ለሥላሴ አስተምህሮ እንደማስረጃ ተደርጎ የሚጠቀሰው አብዛኛውን ጊዜ ከብሉይ ኪዳን ቢሆንም ግን ከኢየሱስ መምጣት በፊት አስተምህሮው በግልፅ ይታወቅ የነበረ አይደለም። ከኢየሱስ ወደምድር መምጣት ብኋላ ግን የሥላሴ አስተምህሮ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንድናውቀው የፈቀደልን በግልፅ ታውቋል።
በአድስ ኪዳን የሥላሴ አስተምህሮ መኖሩን የምንረዳበት አንዱ መንገድ አብ ፡ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በአንድነት የተጠቀሱበት ጥቅስ መኖሩ ነው፦
በአድስ ኪዳን በርከት ባሉ ቦታዎች ላይ ሶስቱም አካላት በግልጽ የተጠቀሱ ሲሆን ይሄ በብሉይ ኪዳን #እኛ በማለት የተነገረው የቁጥር መጠኑ የማይታወቅ የነበረ ቢሆንም የሶስቱ አካላት በግልፅ መጠቀስ #እኛ በማለት በብሉይ በብዛት በቀረበው ማስረጃ የተጠበሱት አካላት ሶስቱ መሆናቸውን ያመለክተናል። ሶስቱም አካላት የተጠቀሱባቸው ጥቅሶች ለምሳሌ፦ (ሜቴ 3:17 ፤ 17:5) ፤ (ማር 9:7) ፤ (ዮሀ 14:15 -16) ፤ (ሮሜ 14:17-18 ፤ 15:16) ፤ (1ኛ ቆሮ 6:11) ፤ (2ኛ ቆሮ 1:21 - 22 ፤ 13:14) ፤ (ኤፌሶን 3:16 - 17) ፤ (1ኛ ተሰ 1:3 - 5) ፤ (2ኛ ተሰ 2:13) ን እናንተ ተመልከቱ። እኛ ግን ልናየው የወደድነው ኢየሱስ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያቱ የሰጠውን ታላቁን ተልእኮ ይሆናል፦
“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ #በአብ_በወልድና_በመንፈስ_ቅዱስ_ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
— ማቴዎስ 28፥19-20
👆 ይህ ታላቅ ተልእኮ አብዛኛውን ጊዜ የሥላሴ አስተምህሮን ለማሳየት የምንጠቀምበት ሲሆነ በዚሁ ልክ ተቃዋሚዎችም ጥቅሱን ለማፈራረስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። እኛም እንደ አስተምህሮው ተከታይነታችን እነሱ ለሚያነሱት ጥቅስ ምላሻችንን በመስጠት አስተምህሯችንን እናፀናለን። ተቃዋሚዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች እና መልሳቸው እንደሚከተለው ቀርቧል፦
#ጥያቄ 1፦" ይሄ ንግግር የኢየሱስ ሳይሆን ቤተክርስቲያን በኒቅያ ጉባኤ (325) የጨመረችው ነው"
# መልስ፦ ይሄንን ጥያቄ ለመመለስ በቀላሉ ከ325ቱ የኒቂያ ጉባኤ በፊት የነበሩት አባቶች ይሄንን አስተምረዋል ወይ? የሚለውን ማየት በቂ ነው።
✟ #የአንፆኪያው አግናጥዮስ ( Ignatius of Antioch) ከ107 - 112 ፅፎታል ተብሎ በሚታሰበው መልእክቱ አንድ ጊዜ ያይደለ ሁለት ጊዜ ይሄንን ጥቅስ ጠቅሶ አሰሰተምሯል፦
“Until He come for whom it is reserved, and He shall be the expectation
of the Gentiles,” have been fulfilled in the Gospel, [our Lord saying,] “👉Go ye and teach
all nations, baptizing them in #the #name of #the #Father, and of #the #Son, and of #the #Holy
Ghost.” ( Ante Nicene fathrs volume 1, pp 221)
"And
again, giving to the disciples the power of regeneration into God,969 He said to them, 'Go
and teach all nations, baptizing them in the name of the Father, and of the Son, and of the
Holy Ghost.'" ( Ante Nicene fathers v 1, pp 1121)
ፅሁፉ እንዳይረዝም ሌሎች ከኒቅያ በፊት የነበሩ አባቶች ፅሁፍ መጥቀሱ አስፈላጊ አይመስለንም። በዚች ማስረጃ ብቻ ጥቅሱ የተጨመረው በኒቅያ ጉባኤ ነው የሚለው ይፈርሳል።
#ጥያቄ 2፦ ኢየሱስ እውነት እንደዛ ካዘዘ ሐዋርያቶቹ ለምን በኢየሱስ ስም ብቻ አጠመቁ?
#✞መልስ፦ ቅዱሳን ሐዋርያት በኢየሱስ ስም ብቻ ማጥመቃቸው ለሁለት ነገር ነው፦
#✞የመጀመሪያው በጊዜው የነበሩ አይሁዶች እንኳን ስለ ሥላሴ ሊረዱ ይቅርና ኢየሱስ ማን እንደሆነ እንኳን በደንብ አልገባቸውም ነበር እና ሐዋርያትም ኢየሱስን እንዲያውቁትና እንዲያምኑበት በኢየሱስ ስም ያጠምቁ ነበር።
#✞ለሁለተኛው ምክንያት ጥቅሱን በደንብ ማስተዋል ይጠይቃል፦
" በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም" በዚህ ንግግር ውስጥ ልብ ማለት ያለብን ነገር "#ስም" የተባለው የአብ ፡ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያቸው ነው። የጋራ መጠሪያቸው ማን ነው? ስንል #እግዚአብሔር የሚለው ነው። አብ እግዚአብሔር ሊባል ይችላል ፡ ወልድና መንፈስ ቅዱስም እንደዛው እግዚአብሔር ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ። በዚህ መሰረት በኢየሱስ ስም ሐዋርያት ሲያጠምቁ የሚያጠምቁት በእግዚአብሔር ነው ማለት ነው። እግዚአብሔር ደግሞ የአንድነት ስማቸው ስለሆነ ሐዋርያት በተዘዋዋሪ በሥላሴ ስም እያጠመቁ ነው ማለት ነው።
#ጥያቄ 3፦አንዳንድ የዋህ ተሟጋቾች ይሄንን ጥቅስ ለሥላሴ ማሳያ የምንጠቀምበት አብ ፡ ወልድ ፡ መንፈስ ቅዱስ የሚለው በተከታታይ ስለተጠቀሰ ብቻ ይመስላቸዋል። እንደዛ ግን አይደለም ከዛ ባለፈ ጥቅሱ አብ ፡ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በመለኮትና በስልጣን አንድ መሆናቸውን ስለሚያሳይ ነው።
እንዴት ነው የሚያሳየው? የሚለውን እንመልከት፦
በመፅሀፍ ቅዱስ #ስም የሚለው ከመጠሪያነት ባለፈ ለእግዚአብሔር ሲውል የእግዚአብሔርን ስም ቅዱስነትና እና ክብር የሚገባው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። ለምሳሌ፦
“#ለስሜ #ክብር #ትሰጡ #ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድድባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፤ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።”
— ሚልክያስ 2፥2
ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው የእግዚአብሔር ስም ክብር የሚገባው ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአድስ ኪዳን ሐዋርያት በኢየሱስ ስም ድንቅ ተአምራትን ሲዳደርጉ እናያለን፦
“ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።”
— ሐዋርያት 3፥6
ይሄ ማለት የአምላክ #ስም አንድን ነገር የማድረግ ኃይል አለው ማለት ነው። መልካም ይሄንን ከያዝን በማቴ 28:19 ያለውን እንመልከተው፦
" በአብ ፡ በወልድ : በመንፈስ ቅዱስ #ስም" ከላይ እንዳልነው ሶሶቱንም አካላት አንድ የሚያደርጋቸው ወይንም የሚጋሩት ስም አለ። የአብ ስም ክብር የሚገባው እንደሆነ ሁሉ ያንን ስም ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንደመጋራታቸው መጠን እነርሱም ከአብ ጋር እኩል ክብር የሚገባቸው ይሆናሉ ማለት ነው። ስም መለኮታዊ ማንነትን የሚገልፅ እንደመሆኑ ደግሞ አብ ፡ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እኩል የሆነ መለኮታዊ ማንነት እንዳላቸው እንረዳለን ።
በተከታታይ መጠቀሱ ደግሞ እነሱ ባሉበት መንገድ ሳይሆን ወልድና መንፈስ ቅዱስ ከአብ ጋር እኩል ትእዛዝ እንደሚሰጡ የሚያመላክተን ነ
ው። በዚህም ብቻ ሳይሆን በጳውሎስ መልእክት በተደጋጋሚ እንደምናየው ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል ፀጋን የመስጠት ሃይል አለው። ለምሳሌ፦
“ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ #ጸጋና #ሰላም ለእናንተ ይሁን።”
— 2ኛ ቆሮ 1፥2
በዚህ ጥቅስ ኢየሱስ ከአብ ጋር እኩል ፀጋን የማደል ስልጣን እንዳለው እንረዳለን። ይሄ ደግሞ ከላይ ካልነው ጋር የሚስማማ ነው። ግን እዚህ ላይ ተቃዋሚዎችን መጠየቅ የምንፈልገው ሌላ አካል ከአብ ወይንም ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ትእዛዝ የሰጠበት ቦታ ካለ እንዲያሳዩን ነው።
08/07/2012 ተጻፈ
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
✞ ወለወላዲቱ ድንግል!
✞ ወለመስቀሉ ክቡር!
✞ ይቆየን!
Comments
Post a Comment