የመንፈስ ቅዱስ አምላክነት


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም!


ከዚህቀደም በተለጠፈው ፅሁፍ ከሶስቱ አካል አንዱ አካል ከሶስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ስለሆነው ስለ መንፈስ ቅዱስ #አካልነት መነጋገራችን ይታወሳል።[ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ነው። ] በዚህ ፅሁፍ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን አምላክነት የምንመለከት ይሆናል። በስላሴ አስተምህሮ ውስጥ አብ ፍፁም አምላክ ወልድም ፍፁም አምላክ መንፈስ ቅዱስም ፍፁም አምላክ ነው። ነገር ግን ሶስት አምላክ አይባሉም ምክንያቱም አምላክነታቸው አንድ ስለሆነ ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስም በመፅሀፍ ቅዱስ እንደተጠቀሰው መለኮታዊነት ያለው አካል ነው። 


     ነገር ግን ተቃዋሚዎች ለምሳሌ የይሆዋ ምስክሮች(Jehovahwitness)መንፈስቅዱስ ዝርው ሃይል እንጅ አካላዊነት ያለውና አምላክ ነው ብለው አያምኑም ነገር ግን መፅሀፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ከሶስቱ አካል አንዱ አካል እንደሆነ እና አምላክም እንደሆነ ይናገራል።

አምላክ ለመሆኑም ዋና መመዘኛችን


1🔺መለኮታዊ ባህሪያት ያለው  መሆኑ።


 ባህሪ ማለት የእግዚአብሄር መገለጫው ማለት ነው። በስላሴነት የሚኖረው እግዚአብሄር የባሕርይ አንድነቱ የሚከተሉት ናቸው፦ ቅድስና፣ ሁሉን አዋቂነት፣ ፅድቅ፣ ፍቅር፣ ሁሉን ቻይነት፣ ምሉዕነት፣ ዘለአለማዊነት ናቸው። እነዚህም ባህርያት ለመንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ጋር አንድ የሚሆንበት፣ የሚተካከልበት ባህርያት ናቸዉ። 

እነርሱም፦

     ✞❶፦ ቅዱስ!መንፈስቅዱስ ቅድስና የባህሪው ነው።


 "ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን #ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።"

(ወደኤፌሶንሰዎች 4:30)

    ✞➋፦ ፃድቅ፦ መንፈስ ቅዱስ ፃድቅ ነው እርሱም እውነት ማለት ነው።


"መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።"(1ኛየዮሐንስመልእክት 5:7)


           ✞❸፦ መንፈስ ቅዱስ በሁሉም ቦታ ይገኛል ፦ በሁሉ ቦታ መገኘት የአምላክ ባህሪ ነው። መንፈስ ቅዱስም በሁሉ ቦታ ይገኛል። 


(መዝሙረዳዊትምዕ.139)

----------

7፤ከመንፈስህወዴት እሄዳለሁ?ከፊትህስወዴት እሸሻለሁ?8፤ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።9፤ እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥


(መጽሐፈኢዮብምዕ.33)

----------

4፤#የእግዚአብሔር_መንፈስ_ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ። 



      ✞❹፦ #መንፈስ_ቅዱስ_አዕማሬ_ኩሉ_ነው። አዕማሬ ኩሉ ማለት ሁሉን አዋቂ(omniscient)ማለትነው። መንፈስ ቅዱስም የልብን ሁሉ ያውቃል፦ 


"...መንፈስምየእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር #ሁሉን_ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።"(1ኛወደቆሮንቶስ ሰዎች 2:10)

ሁሉንስለሚያውቅሁሉን ያስተምራል

"...አብበስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ #ሁሉን_ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።"(የዮሐንስወንጌል14:26)

"...የምነግራችሁገና ብዙ አለኝ፥ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም።

13፤ ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።"

(የዮሐንስወንጌልምዕ.16)


  ✞❺፦ #መንፈስ_ቅዱስ_ሁሉን_ቻይ_ነው።


"...መልሶም።ለዘሩባቤል የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። "(ትንቢተዘካርያስ4:6)


"...#የእግዚአብሔር_መንፈስ_ፈጠረኝ፥#ሁሉንም_የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።" (መጽሐፈኢዮብምዕ.33)


      ✞❻፦ #መንፈስ_ቅዱስ_ፈጣሪ_ነው፦ 

እግዚአብሔር አምላክ አለማትን በሙሉ እንደፈጠረ በቅዱሳት መፃህፍት የተጠቀሰ ጉዳይ ነው መንፈስ ቅዱስም ፈጣሪ ነው ሲባል ከአብ ከወልድ የተለየ ፈጣሪ ሳይሆን ከአብ ከወልድ ጋር የተካከለ መሆኑን ነው የሚያሳየን። 


"...#የእግዚአብሔር_መንፈስ_ፈጠረኝ፥#ሁሉንም_የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ።" (መጽሐፈኢዮብምዕ.33)


      ✞❼፦ መንፈስ ቅዱስ ዘለአለማዊ ነው፦ ዘለአለማዊ 


"14፤ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ..."

(ወደዕብራውያን9:14፤)

🏁መንፈስቅዱስመለኮታዊ ባህርያት ሁሉ ያሉት ሶስተኛ አካል የሆነ ከአብ ከወልድ ጋር በአንድነት የሚመለክ እግዚአብሔር ነው።


2🔺እግዚአብሔር መባሉ።

     እግዚአብሔር የሚለው የአምላካችን መጠሪያ ለሶስቱም አካላት ውሏል ማለትም ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ። 

ለምሳሌ


ለአብ፦ "...ስምዖንጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።"

(የማቴዎስወንጌል16:16)እዚህጋር እግዚአብሔር የተባለው አብ ነው።


ለወልድ፦ " ...በመጀመሪያውቃልነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።"(የዮሐንስወንጌል1:1)እዚህጋር ኢየሱስ ክርስቶስ ከስጋዌ በፊት(ከስጋዌቡሃላምቃል ነው)ቃልእግዚአብሔር ተብሏል።


እንዲሁም ለመንፈስ ቅዱስ ከዚህ በታች ባለው ክፍል ተጠቅሷል። ሐንንያ ያታለለው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው።


3፤ ጴጥሮስም። ሐናንያ ሆይ፥ #መንፈስ_ቅዱስን_ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ?4፤ ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን?ከሸጥኸውስበኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን?ይህንነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ?#እግዚአብሔርን_እንጂ_ሰውን_አልዋሸህም_አለው።

(የሐዋርያትሥራምዕ.5)


"...#የእግዚአብሔር_ቤተ_መቅደስ_እንደ_ሆናችሁ#የእግዚአብሔርም_መንፈስ_እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?"(1ኛወደቆሮንቶስ ሰዎች 3:16)

እኛክርስቲያኖችቤተ መቅደስ ስንባል የእግዚአብሔር ማደሪያዎች መሆናችንን የሚያመለክት ነው። ያም የሚያድርብን አንዱ አካልም መንፈስ ቅዱስ ነው ስለዚህ  መንፈስ ቅዱስ በዚህ ቦታ እግዚአብሔር ተብሏል።


3🔺በብሉይ ኪዳን የተናገረው እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን ለመንፈስ ቅዱስ ሲነገር እንመለከታለን ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፦


⓵፦ መስማትን ትሰማላችሁ ያለው መንፈስ ቅዱስ ነው።


በኢሳይያስ እግዚአብሔር መስማትን ትሰማላችሁ...እያለየተናገረው በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተገልጿል።


(ትንቢተኢሳይያስምዕ.6)

----------

8፤የጌታንምድምፅ። ማንን እልካለሁ?ማንስይሄድልናል?ሲልሰማሁ። እኔም። እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።9፤ እርሱም። ሂድ፥ ይህን ሕዝብ። መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም በላቸው። 10፤ በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፥ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፥ ጆሮአቸውንም አደንቍር፥ ዓይናቸውንም ጨፍን አለኝ።

➞አዲስ ኪዳን!

(የሐዋርያትሥራምዕ.28)

----------

25፤እርስበርሳቸውም ባልተስማሙ ጊዜ፥ ጳውሎስ አንዲት ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ እንዲህም አለ። #መንፈስ_ቅዱስ_በነቢዩ_በኢሳይያስ_ለአባቶቻችን።26፤ ወደዚህ ሕዝብ ሂድና። መስማትን ትሰማላችሁና አታስተውሉም፥ ማየትንም ታያላችሁና አትመለከቱም፤27፤ በዓይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዓይናቸውንም ጨፍነዋል በላቸው


⓶፦ እስራኤላውያን በምድረ በዳ ያስቆጡት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ


(መዝሙረዳዊትምዕ.95)

----------

6፤ኑ፥እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ፤7፤ እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና።8፤ በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑት እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ። 9፤ የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ ፈተኑኝ ሥራዬንም አዩ።


ይህ ክስተት በዘፀአት ላይ የሚገኝ ነው እንዲህም ይላል፦"...ሕዝቡምሙሴንተጣሉት። የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም። ለምን ትጣሉኛላችሁ?እግዚአብሔርንስለምን ትፈታተናላችሁ?አላቸው።"

(ኦሪትዘጸአት17:2፤)


መዝሙረኛውእስራኤላውያንእግዚአብሔርን በምድረ በዳ እንደተፈታተኑት ከዘጸአት ጠቅሶ ነግሮናል። ይህ ያህዌ እግዚአብሔርም ማን እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ አስቀምጦልናል። እርሱም መንፈስ ቅዱስ ነው።



(ወደዕብራውያንምዕ.3:7-9)

-"...ስለዚህመንፈስ ቅዱስ እንደሚል። ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት፥ አባቶቻችሁ እኔን የፈተኑበት የመረመሩበትም አርባ ዓመትም ሥራዬን ያዩበት በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማስመረር እንደ ሆነ፥ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።


⓷፦ ቅዱሳት መፃህፍት እንዲፃፉ ነብያትን የሚያናግር እርሱ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፦ 


1፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። 2፤ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስማ፥ ለይሁዳም ሰዎች በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ #ተናገር፥

➞(ትንቢተኤርምያስምዕ 11:1-2)


ነብዩኤርምያስን እንዲናገር የሚነዳውና የሚነግረው እግዚአብሔር እንደሆነ በቁ.1ተቀምጧል፤ በአዲስ ኪዳን ስንመጣ ያ ነብዩ ኤርምያስንና ሌሎቹን ነብያት እያናገረ ቅዱሳት ቃሉን የሚያፅፍና የሚያናግረው መንፈስ ቅዱስ መሆኑ ተቀምጦልናል።


“...ትንቢትከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።” ➞(2ጴጥ1:21)


ቅዱሳትትንቢቶችንየሚያፅፈው እና የሚያስነግረው እርሱ እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስ ነው።


⓸፦ በኤርምያስ አዲስ ቃል ኪዳንን እገባለሁ ያለው እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን መንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ፦ 


(ትንቢተኤርምያስምዕ.31)

32፤ከግብጽአገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር። 33፤ ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። 34፤ እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን። እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና። 


በኤርምያስ ትንቢት ቃል ኪዳንን እገባለሁ አለ የተባለው እግዚአብሔር በአዲስ ኪዳን ያን ቃል የተናገረው እርሱ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በግልፅ ተቀምጧል።


➞(ወደዕብራውያንምዕ.10)

15-16፤መንፈስቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል፤ ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ 17፤ ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል።


🏁ማጠቃለያ፦ መንፈስ ቅዱስ ከሶስቱ አካል አንዱ አካል ነው፣ እግዚአብሔርም ነው። መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው ሲባል አብ አይደለም ወልድም አይደለም ለዚህም ጥሩ ዋቢ የሚሆነን፦ 

"...ወደእኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ #አሁንም_ጌታ_እግዚአብሔርና_መንፈሱ_ልከውኛል።"➞(ትንቢተኢሳይያስ48:16)እግዚአብሔርእና መንፈሱ ብሎ ሁለት አካላት መሆናቸውን ከለየልንና እነዚህም አካላት ወልድን ከላኩ በዚህ ቦታ ሶስት አካላት ያሉ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብ ነው ወልድ ነው ለሚሉ የonly jesus አስተምህሮዎች ትልቅ ጥያቄን ይፈጠራል።  እኛ ከዚህ በፊት ይህን ጥቅስ ያብራራንበት ፖስት እነሆ [ ኢሳያስ 48 በአንድ ድንጋይ ሶስት ወፍ ]


መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር


ክፍል ሶስት [ አፅናኙ መንፈስ ቅዱሰ ነው ]

___________________✝

ለማንኛውም አስተያየት፦

[ ዐቃቢያነ እምነት ዘኦርቶዶክስ ]

ለቴሌግራም ቻናላችን፦

[ ዕቅበተ እምነት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ]

     

Comments

Popular posts from this blog

ዕቅበተ እምነት

ወላዲተ አምላክ

መልስ ለወሒድ ዑመር