Posts

የኡስታዙ ውዝግብ

  የእግዚአብሄር ፍጥረት የመጀመሪያው ማነው? ጉማሬ? ሰማይናምድር? ወይስ ኢየሱስ? ብሎ ድንክርክር ላለው ኡስታዝ ወሒድ የተሰጠ መልስ! ይህ ሰው እራሱን የግሪክ እና የእብራይስጥ አስተማሪ አድርጎ የሾመ ሰው ሲሆን ይህን ተገን አድርጎ ሙግቶችን በእነዚህ ቋንቋዎች የሚያቀርብ ሰው ነው። ለጠየቀውን ጥያቄ ከዚህ በታች የእርሱንም እውቀት እየገመገምን እንመልከተው፦  ጥያቄውም፦ የእግዚአብሄር ፍጥረት የመጀመሪያው ማነው? ጉማሬ? ሰማይናምድር? ወይስ ኢየሱስ? በመጀመሪያ ይህን ጥያቄ ለምን እንደተነሳ ከታች የምናየው ቢሆንም ጥያቄው የተነሳው መፅሀፍ ቅዱስን ጠንቅቆ ካለመረዳትና ከድርቅና የሆነ እንጅ እግዚአብሄር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን እንደፈጠረ በዘፍጥረት 1:1 ላይ በግልፅ " እግዚአብሔር መጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ " ተብሎ የተነገረ ሲሆን ጠያቂው ግን ይህን እንዳላዩ አልፎ በእሱ ሀሳብ መጀመሪያ ተፈጠሩ የሚላቸውን የመፅሀፍ ቅዱስን ቃል በማጣመም አስቀምጧል።  በመቀጠልም... A-ጉማሬ፦  ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፤ መጽሐፈ ኢዮብ 40 : 15 እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው፤ መጽሐፈ ኢዮብ 40 : 19  He [is] the chief of the ways of God: he that made him can make his sword to approach [unto him]. Job 40 : 19 አውራ ተብሎ የተቀመጠው ቃል መጀመሪያ the first የዕብራይስጡ ደግሞ "ረሺት" ማለት ሲሆን ለሰማይና ምድር መጀመሪያነት ተጠቅሷል።] መልሴ፦ በመጀመሪያ "רֵאשִׁ֤ית"(reshit) የምትለው ቃል የፍጥረትን መጀመሪያ ለመጥቀስ ብቻ የምትውል ናት የሚል ድምዳሜ በዕብራይስጥ የቋንቋ ህግ የለም አይኖርምም። እ

የድንግል ማርያም ትንሳኤና እርገት

 " ዕርገተ ማርያም"         አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!     የክርስቶስ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን!  ተወዳጅ የቻናላችን ቤተሰቦች በመጀመሪያ እናኳን ለፍስለታ ለማርያም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!   ዛሬ እግዚአብሔር ከፈቀደ በማርያም ፍስለተ ስጋ ላይ ትንሽ ነገርን ለማለት ፈልገን ነው ያው በርካታ ወንድሞች ፅፈውበታል አብራርተውታልም ግን ደግሞ እኛም የምናምነውን መመስከር ይገባናልና ትንሽ ነገር ለማለት ወደድን እስኪ አንዳንድ ጥያቄዎችን እያነሳን እንይ፦  📌  ጥያቄ ➊፦        “ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።”  — ዮሐንስ 3፥13      " ይህ ቃል እንደሚነግረን ወደሰማይ ሊያርግ የሚችለው ኢየሱስ ብቻ ነው ስለዚህ ማርያም አርጋለች የሚለው የለየለት ክህደት ነው" ለሚሉት፦    ይህን አመክንዮ የሚያነሱ ፕሮቴስታንት ወይንም ተሐድሶ ወንድሞች ሁለት ነገሮችን ዘንግተዋል እኒህ ነገሮች ደግሞ እንዲህ ለስህተት ዳርገዋቸዋል። የዘነጓቸው ሁለት ነገሮች፦ ➊፦ ገና ከጅምሩ ይህንን አመክንዮ ስህተት የሚያደርገው ነገር ቢኖር እነርሱ እንደሚሉን ወደሰማይ ያረገው ኢየሱስ ብቻ ከሆነ መፅሀፍ እርስ በራሱ ይጋጫል ወደሚል ድምዳሜ ማምራታችን ነው ምክንያቱም መፅሀፍ ሄኖክና ኤልያስ ወደሰማይ አርገዋል ይለናልና፦         “ሲሄዱም፦ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።”— 2ኛ ነገሥት 2፥11       “ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታ

አማኑኤል ተብሎ የተጠራበትን ቦታ አሳዩን❓

 አማኑኤል ተብሎ የተጠራበትን ቦታ አሳዩን❓      አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!      ብዙ ጊዜ ስለ ኢየሱስ አምላክነት የተተነበየበትን የብሉይ ኪዳን ትንቢት ለማሳየት ከምንጠቅሳቸው ጥቅሶች መካከል ኢሳይያስ 7:14 አንዱ ሲሆን ይህንን ጥቅስ ስንጠቅስ ሙስሊሞችም ሆኑ አይሆዱች ይህንን ጥቅስ ለመቃዎም አንድ ሁለት ሙግቶችን ያነሳሉ። አንዱን ሙግታቸውን እግዚአብሔር ቢወድና ቢፈቅድ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን ብለን ቀጠሮ እንያዝና ከሁለቱ እየተዘወተረ የሚነሳውን አንዱን " ትንቢቱ  ' ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ' ነው የሚለው ይህ ትንቢት ስለ ኢየሱስ ከሆነ ኢየሱስ አማኑኤል ተብሎ የተጠራበት ቦታ የት አለ?" የሚለውን ለዛሬ እንመለከታለን ።     ወደ መልሱ ስንገባ ይህ ሙግታቸው ውሃ የማያነሳበትን ሁለት ምክንያት በማስቀመጥ ምላሻችንን እንቋጫለን፦   ➊፦ ትንቢቱ የተፃፈው በአይሁድ ልማድ ነውና በእነርሱ ልማድ መሰረት ለአንድ አካል ስም ሲሰጥ የግድ በዛ ስም መጠራት አለበትን? የሚለውን አስቀድመን እንመልከት።    በጊዜው በነበሩ አይሆዶች ለአንድ አካል ጊዜውን እና ሁኔታዎችን ያገናዘበ ወይንም ደግሞ የተሰየመው አካል ሊያሟላው የሚችል የተለያየ ስም መስጠት የተለመደ ነው ግን ይህን የተለያየ ስም ሲሰጡ የግድ በዛ ስም ይጠራ የሚል መርህ የላቸውም። ይህንን ለማሳየት ሶስት ምሳሌዎችን ልጥቀስ፦ #1ኛ፦ በዚሁ በትንቢተ ኢሳይያስ 8 : 3 ላይ ነቢዪቱ ልጅን እንደምትወልድ ስሙንም " ማሄር ሻላል ሃሽ ባዝ(ምርኮ ፈጠነ ፤ ብዝበዛ ቸኮለ)" ብለው እንዲጠሩት ይናገራል፦   “እኔም ወደ ነቢዪቱ ሄድሁ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እግዚአብሔርም፣ እንዲህ አለኝ፤ “ስሙን ማኸር-ሻ

ከአንድ በላይ ጋብቻ ከመፅሀፍ ቅዱስ!

*ከአንድ በላይ ጋብቻ በመፅሀፍ ቅዱስ... *       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም!      እስልምና ሀይማኖትን ከምንተችበት አስተምህሮዎቹ መካከል አንድኛው " አንድ ወንድ አራት ሴት ማግባት ይችላል" የሚለው ነው። ይህን  ህሊና ላለው ወንድ እና ይሄ እጣ ለደረሰባቸው ሚስቶች የከበደ ሸክም ቀለል ለማድረግ ሲባል ሙስሊሞች "እከክልኝ ልከክልህ" አይነት ሙግትን ያነሳሉ።  ሙስሊሞች" እንደት አንድ ወንድ ለአራት ሴት ይፈቀዳል?" ተብለው ሲጠየቁ  " በእናንተስ መፅሀፍ አንድ ለአንድ የተባለው የት ነው? በሙሴ ህግስ ከአንድ በላይ ትዳር ተፈቅዶ የለምን? በመፅሀፍ ቅዱስስ ከአንድ በላይ ያገቡ ሰዎች አሉ አይደለም ወይ?" በማለት የእናንተም ይፈቅዳል ስለዚህ ልክ ነው የሚል ስሁት ሙግት ያቀርባሉ። ይኼንን ሙግታቸውን ከአመክንዮ(logic) አንፃር ካየነው "you too fallacy " በሚል የfallacy ጎራ የሚመደብ ነው። በአለማዊ የ philosophy ትምህርት ይሄ አመክንዮአቸው ስህተት መሆኑ ከተመሰከረባቸው በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ሀሳባቸውን እስኪ እንመዝነው፦  ➊   መፅሀፍ ቅዱስ አንድ ለአንድን ያዛልን? የሚለውን እናስቀድምና ፣           ፨ ከብሉይ ኪዳን           ፨ ከአድስ ኪዳንና           ፨ ከሚስጥራዊ መልእክቱ ተነስተን ማስረጃዎችን እናቅርብ፦ ✟  #ከብሉይ_ኪዳን፦   ትዳር ወይንም ጋብቻ በሰው ፈቃድ የተመሰረተ ሳይሆን እግዚአብሔር እራሱ ከፍጥረት መጀመሪያ የመሰረተው የተባረከ ግንኙነት ነው። እግዚአብሔር አዳምን ፈጥሮ አልተወውም አጋዥ የምትሆነውን ሔዋንን ከጎኑ አበጅቶለታል።   ይሄ የእግዚአብሔር ፍጥረት እንደሚያስረ

ወላዲተ አምላክ

 ወላዲተ አምላክ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ : በወልድ : በመንፈስ ቅዱስ ስም!        በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሰረት አካላዊ ቃል እግዚአብሄር ወልድ ለሰው ልጆች ሁሉ ድህነት ሲባል ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆኗል። (የዮሀንስ ወንጌል 1:1-4) ስለዚህ ከድንግል ማርያም የተወለደው አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ ድንግል ማርያምን የአምላክ እናት እንላታለን! የአምላክ እናት!      የአምላክ እናት (Theotokos) የሚለው የቃሉ ምንጭ (ጥንት የመጣው) ከግሪኩ Theotokos ትርጉሙም የእግዚአብሔር እናት፣ የአምላክ እናት አምላክን የወለደች ማለት ነው። ይህ ቃል የሚገልጸው ዋና ሃሳብም ከቅድስት ድንግል ማርያም ሰው የሆነውና የእኛን ባህርይ ከሀጥያት በስተቀር ተካፍሎ በስጋ የተገለጠው ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው የሚለውን የክርስትና መሰረተ እምነት የያዘ እና መሰረት ያደረገ ነው። ይህ ስያሜም በአጽንኦት የሚገልጸው እመቤታችን ድንግል ማርያም የወለደችው ሕጻን "ዕሩቅ ብዕሲ" ሰው ብቻ አለመሆኑን ይልቁንም የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ መሆኑን ነው።          ከእመቤታችን ከድንግል ማርያም ተጸንሶ የተወለደው አዲስ "ወልድ" አይደለም ዘለዓለማዊውና ቀዳማዊው የእግዚአብሔር አብ የባህርይ ልጅ አካላዊ ቃል የሰውን ባህርይ ገንዘቡ አድርጎ ራሱ ሰው ሆነ እንጅ ለዚህም ነው በትንቢተ ኢሳይያስ 9:6 ላይ ከድንግል ማርያም የተወለደው ሕጻን ሃያል አምላክ እና ዘለዓለማዊ አምላክ ነው የሚለን። የእመቤታችን የአምላክ እናትነትን እዚህ ጋር መረዳት እንችላለን። ከእርሷ የተወለደው እርሱ ሰው የሆነ አምላክ ከሆነ እርሷ ደግሞ ሃያል አምላክ ለሆነው ለተወለደው ሕጻን እናት መሆኗ ግልጽ ነው። እርሱም አምላክ እንደመሆኑ

መልስ ለወሒድ ዑመር

 መልስ ለወሒድ ዑመር ሃይማኖተ አበው ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነው ይላልን?      ወሒድ ዑመር ሃይማኖተ አበው  የተባለው የቤተክርስቲያን መጽሐፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጡር ነው ይላል ብሎ ትልቅ የቅጥፈት ፅሁፍ ፅፎ አስነብቦናል። ሃይማኖተ አበው የተባለው መጽሐፍ በይበልጥ ምሥጢረ ሥላሴን እና ምሥጥረ ሥጋዌን (ነገረ-ክርስቶስን) የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ ቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶች( Early Church Fathers) ለመናፍቃን እና ለከሃድያን የሰጡትን ምላሾች እና ተግሳጾችን አሰባስቦ የያዘ ነው። እስቲ የወሒድ የስህተት ሀሳቦችን እንመልከት! =>>>ወሒድ " የተፈጠረ ነገር ሁሉ ላይወለድ ይችላል፥ ለምሳሌ መላእክት ተፈጥረዋል ግን አልተወለዱም። ግን የተወለደ ነገር ሁሉ ከመወለዱ በፊት በማኅጸን ይፈጠራል። ኢየሱስ ማርያም ማህፀን ውስጥ መፈጠሩን በተለይ የክርስትና የዐቂዳህ መጽሐፍ የሆነው ሃይማኖተ-አበው ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት በማህጸን ውስጥ የተፈጠረ “ፍጡር” ነው ይላል፦" =>>>ምላሽ ወሒድ " የተወለደ ሁሉ አስቀድሞ በማህጸን ይፈጠራል " በማለት የኢየሱስ ሕልውና የጀመረው በድንግል ማርያም ማህጸን ውስጥ እንደሆነ አድርጎ ያስቀምጣል። ኢየሱስ በማህጸን ተፈጠረ የሚለው የወሒድ ሀሳብ የኢየሱስ ሕልውና በማህጸን የተጀመረ እንደሆነ የሚናገር ነው። መክንያቱም መፈጠር ማለት ካለ መኖር ወደ መኖር መምጣት ነው።ከዚያም ከሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ማስረጃ ብሎ የተወሰኑ ጥቅሶችን ጠቅሷል። ወሒድ ከሃይማኖተ አበው እራሱ ሲጠቅስ በትክክል አይጠቅስም። ለምን እንደዚህ እንዳልኩ ከታች እንመለከተዋለን። ወሒድ ወደ ጠቀሳቸው ጥቅሶች ከማለፋችን በፊት እሱ እራሱ የጠቀሳቸው አባቶች ውስጥ ስለ ኢየሱስ ቅድመ ህልውና(ከ

ኢሳይያስ 48:16

 በ 1 ድንጋይ ሶስት ወፍ= 1 ጥቅስ ለሶስት የሃይማኖት ተቋማት       አንድ አምላክ በሚሆን በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም       በዚህ ጽሁፍ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በአንድት የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ሶስት የተለያዩ የሃይማኖት  ተቋማት በኢየሱስ ላይ ያላቸውን አመለካከት ኢትዮጵያ ግብፅን ዶጋሊ ላይ በደቂቃዎች የዶግ አመድ እንዳደረገቻት እኛም በደቂቃዎች የእነርሱን እምነት የዶግ አመድ እናደርገዋለን💪 😁       መልስ የምንሰጥባቸው ሶስቱ የሃይማኖት ተቋማት፦  1፡ እስልምና 2፡ only Jesus እና 3፡ የይሖዋ ምስክሮች ይሆናሉ ። (ጽሁፉ ሊረዝም ስለሚችል በሰከነ መንፈስ እንዲታነቡት እጠይቃለሁ )    እኒህ ሶስቱ የእምነት ድርጂቶች እንደሚታወቀው  እርስ በእርስ የተለያዩ ሲሆኑ  እስልምና፦ ኢየሱስ መለኮታዊ ክብር የለውም የሚሉ ሲሆን  የይሖዋ ምስክሮች ደግሞ ፦ኢየሱስ መለኮታዊ ክብር ያለው ቢሆንም ከእግዚአብሔር አብ ጋር ግን የተስተካከለ (እኩልክብር ያለው) አይደለም ብለው የሚያምኑ ናቸው።    Only Jesus ቤተ እምነት ደግሞ ፦ኢየሱስ እና እግዚአብሔር ወልድ የተለያዩ አካላት ሳይሆኑ አንድ አካል ናቸው። ኢየሱስ እግዚአብሔር አብ የተገለጠበት ስጋ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው።      ሶስቱንም የሚያመሳስላቸው ነገር ደግሞ ሶስቱም ቤተ እምነቶች Unitarian መሆናቸው ነው። እንደ እነርሱ እምነት የምስጢረ ሥላሴ አስተምህሮአችን ስህተት ነው ባይ ናቸው። ከዚህ በመነሳት መልስ የምንሰጥባቸው ነገሮች 4 ናቸው ማለት ነው።  መልካም ወደ መልሱ እንሂድ፦       መልስ ለመስጠት የምንጠቀምባት አንዲት ጥቅስ በነብዬ እግዚአብሔር ኢሳይያስ መፅሀፍ ላይ የተቀመጠችው ትሆናለች፦       “ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በ